ፖለቲካ
የቀድሞው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ ውስጥ ህይወታቸው አልፏል
ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆና ያገለገሉት አሊ ካሊፍ ጋላይድ በ79 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋላይድ ከእርስ በእርስ ግጭት ማብቂያ ቀጥሎ በጅቡቲ ከተደረገው መደበኛ ጉባዔ በኋላ ነበር የተሸሙት
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋላይድ ከእርስ በእርስ ግጭት ማብቂያ ቀጥሎ በጅቡቲ ከተደረገው መደበኛ ጉባዔ በኋላ ነበር የተሸሙት
ከእርስ በእርስ ጦርነት በኋላ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆና ያገለገሉት አሊ ካሊፍ ጋላይድ በ79 ዓመታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ህይወታቸው አልፏል፡፡
የሀገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ እስማኤል ሙክታር የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ይኖሩበት በነበረው በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ መሞታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ፕሮፌሰር ጋላይድ እ.ኤ.አ በ2000 የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን በፕሬዚዳንት አብዲ ቃሲም ሳላም ነበር የተሸሙት፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋላይድ ከእርስ በእርስ ግጭት ማብቂያ ቀጥሎ በጅቡቲ ከተደረገው መደበኛ ጉባዔ በኋላ ነው ሹመቱ የተሰጣቸው፡፡
በጅግጅጋ ህይታቸው ያለፈው የቀድሞው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር የምክር ቤት አባል የነበሩ ሲሆን በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎችም ሲያስተምሩ እንደነበር ጎብጆብ ኒውስ ዘግቧል፡፡