ተመድ ለ400ሺ የሶማሊያ ህጻናት የፖሊዮና ኩፍኝ ክትባት ልሰጥ ነው አለ
ከአመቱ መጀመሪያ ጀምሮ 744 ህጻናት በኩፍኝ በሽታ መጠቃታቸው ሪፖርት ተደርጓል
የዓለም ጤና ድርጅት በሶማሊያ የሶስት ቀናት የክትባት ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ገለጸ
የዓለም ጤና ድርጅት በሶማሊያ የሶስት ቀናት የክትባት ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ገለጸ
በሶማሊያ እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች ለሆኑ 400ሺ ህጻናት የፖሊዮና ኩፍኝ ክትባት ለመስጠት የሶስት ቀናት ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅትና በዩኒሴፍ የሚመራው ይህ ጥረት በኮሮና ቫይረስ እየተጠቃች ባለችው የሞቃዲሹዋ ባንዲር የሚገኙ ህጻናትን ኢላማ አድርጓል፡፡ ከአመቱ መጀመሪያ ጀምሮ 744 ህጻናት በኩፍኝ በሽታ መጠቃታቸው ሪፖርት ተደርጓል፡፡
ባንዲር በሶማሊያ የተፈናቀሉ ሰዎች የሚገኙባትና አለምአቀፍ ጉዙ ለሚያደርጉ ሶማሊያውን መናኸርያም ነች፡፡ ግዛቷ በፖሊዮ የተጠቁ ሶስት ህጻናትም የተገኙባት መሆኗ ተረጋግጧል፡፡ በሶማሊያ ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ ሁለት አይነት የፖሊዮ ቫይረስ እየተሰራጨ መሆኑና 19 ህጻናትን የአካል ጉዳተኛ ማድረጉ ታውቋል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት የፖሊዮ ፕሮግራም የሶማሊያ ተወካይ ዶክተር አስማ አሊ በሶማሊያ ያለውን የጤና እንቅስቃሴ ጀምረውታል፡፡
“ይህ ዘመቻ ባለፈው አመት ህዳር ወር ሊካሄድ የታሰበ ቢሆንም በቴክኒካል ችግር ምክንያት ወደ ፈረንጆቹ 2020 ሊዛወር ችሏል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ የኮሮና ወረርሽኝ መጣና ነገሩን አበላሸው፡፡ ነገርግን አሁን ብዙ ህጻናትን የበሽታ መከላከል አቅም ለማሳደግ እድል አግኝተናል”ሲሉ ዶክተር አስማ አብራርተዋል፡፡
የዩኒሴፍ የጤና ኃላፊ ፔኖሎፕ ካምቤል የሶማሊያ ዩኒሴፍ የኮሮና ዘመቻ ይቀጥላል፤ በተመሳሳይ መልኩ የክትባቱ ስራ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ኩፍኝና ፖሊዮ በክትባት የሚድኑ በሽታዎች ስለሚሆኑ እነዚህን ወረርሽኖች ማስቆም እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡