የኢታማዦር ሹሙ ሴት ልጅ እና ሹፌራቸው ተገድለዋል
የኡጋንዳ የቀድሞ የመከላከያ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ካቱምባ ዋማላ ዛሬ ጠዋት ሦስት ሰዓት ገደማ በሞተር በታጀቡ ታጣቂዎች የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡ በታጣቂዎቹ ደረታቸው ላይ ሁለት ጊዜ በጥይት የተመቱት ጄኔራሉ በአሁኑ ሰዓት ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ጄነራሉ በጥይት መመታታቸውን ተከትሎ ከመኪናቸው በደም ተጨማልቀው መውጣተቸውና በካምፓላ ወደ ሚገኝ አንድ ሆስፒታል ተወስደው እየታከሙ መሆኑ ነው የተገለፀመው፡፡
በግድያ ሙከራው አብሮአቸው የነበሩ ሴት ልጃቸውና ሾፌራቸው መግደለቸውን ኤንቢኤስ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ጄኔራሉ ወላጅ እናታቸው አርፈው ለቀብር እየሄዱ ባሉበት ወቅት ነው ጥቃቱ የተፈጸመባቸው፡፡
ጀነራል ካቱምባ ዋማላ አሁን ላይ የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ናቸው፡፡