ጀርመን ከውድድር መጀመር ቀደም ብሎ 1400 ሰዎች ያለፈቃድ ወደ ግዛቷ መግባታቸውን አስታወቀች
በዚህ ውድድር የ23 የአውሮፓ ሀገራት የወንዶች እግር ኳስ ቡድኖች ተሳታፊ ተሳታፊ ሆነዋል
ጀርመን የውድድሩን ደህንነት ለማረጋገጥ ቢያንስ 22ሺ ወታደሮችን እያሰማራች ትገኛለች
ጀርመን የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ከመጀመሩ ቀደም ብሎ 1400 ሰዎች ያለፈቃድ ወደ ግዛቷ መግባታቸውን አስታወቀች
የአውሮፓ ዋንጫ አስተናጋጅ የሆነችው ጀርመን የድንበር ተቆጣጣሪ ባለልጣናት ውድድሩ ከመጀመሩ ከሳምንት በፊት 1400 ሰዎች ያለፈቃድ መግባታቸውን እና 173ቱ የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው አስታውቋል።
ውድድሩን በማስመልከት በጊዜያዊነት ቁጥጥሩን ያጠናከረው ፓሊሰ ከፈረንጆቹ ሰኔ 7-13 ባለው ጊዜ ውስጥ በህገወጥ መልኩ ወደ ሀገሪቱ ሊገቡ የነበሩ 900 ሰዎችን ማስቆሙን ገልጿል።
"ይህ ማለት እየወሰድን ያለነው እርምጃ ይሰራል ማለት ነው። ከሁሉ በላይ ነውጠኞችን ለመለየት እና እንዳይገቡ ለማድረግ ይረዳናል" ሲሉ የሀገር ውስጥ ሚኒስተሩ ናንሲ ፌይሰርን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
ጀርመን የውድድሩን ደህንነት ለማረጋገጥ ቢያንስ 22ሺ ወታደሮችን እያሰማራች ትገኛለች። ፋይሰር እንደገለጹት ከሆነ ይህ በሀገሪቱ ታሪክ ትልቅ ስምሪት ነው ብለዋል።
ሀገሪቱ አሁን ላይ ቁጥጥር እያደረገችው ያላቸው ሰዎች በሸንገን ቪዛ አማካኝነት በነጻ በሚንቀሳቀሱበት ከዴንማርክ እና ከፈረንሳይ በሚያዋስኗት ቦታዎች ነው።
በሸንገን ቦታዎችም እስከ ሐምሌ 19 ድረስ ጊዜያዊ ቁጥጥር እያደረገች ነው።
በአውሮፓ እግርኳስ ትልቁ ውድድር በጀመርን አስተናጋጅነት መካሄድ የጀመረው ከቀናት በፊት ነው።
በዚህ ውድድር የ23 የአውሮፓ ሀገራት የወንዶች እግር ኳስ ቡድኖች ተሳታፊ ተሳታፊ ሆነዋል።