ቦትስዋና ጀርመን 20ሺ ዝሆኖችን እንድትወስድላት ጠየቀች
130ሺ ዝሆን ያላት በትስዋና በዝሆን ቁጥር ብዛት ከዓለም 1/3ኛውን ትሸፍናለች
የቦትስዋናው ፕሬዝደንት ሞክግዊሲ ማሳሲ በሀገሪቱ በደተረገው የጥበቃ እና እንክብካቤ ስራ የዝሆኖች ቁጥር ጨምሯል ብለዋል
ቦትስዋና ጀርመን 20ሺ ዝሆኖችን እንድትወስድላት ጠየቀች ።
የቦትስዋናው ፕሬዝደንት ሞክግዊሲ ማሲሲ በሀገሪቱ በደተረገው የጥበቃ እና እንክብካቤ ስራ የዝሆኖች ቁጥር ጨምሯል ብለዋል።
ቢቢሲ የጀርመን መገናኛ ብዙኻንን ጠቅሶ እንደዘገበው ፕሬዝደንቱ የዝሆኖች ቁጥር መጨመር በሀገሪቱ ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ተናግረዋል።
"ልትነግረን እንደሞከርከው ጀርመኖች ከእንሳት ጋር ይኖራሉ" ሲሉ ማሲሲ ብሊድ ለተሰኘው የጀርመኑ ጋዜጣ ተናግረዋል።
130ሺ ዝሆን ያላት በትስዋና በዝሆን ቁጥር ብዛት ከዓለም 1/3ኛውን ትሸፍናለች።
ፕሬዝደንቱ የዝሆን መንጋ እህል እያወደመ እና በንብረት ላይ ጉዳት እንደሚያደርሰ ነው ብለዋል።
ቦትስዋና የሀገሪቱን የዝሆን ቁጥር ለመቀነስ ቀደም ሲል እንደ አንጎላ ለመሳሰሉት ሀገራት 8ሺ ዝሆኖች መስጠቷን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ዝሆኖችን ደግሞ ለሞዛምቢክ መስጠቷ ይታወሳል።
የዝሆን መንጋ በንብረት እና በሰው ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የገለጹት ማሳሲ "ለጀርመን እንዲህ አይነት ስጦታ መስጠት እንፈልጋለን" ብለዋል።
ቦትስዋና በፈረንጆቹ 2014 አደን እንዳይደረግ እግድ ጥላ የነበረ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ ባሳደረው ጫና ምክንያት በ2019 እግዱን አንስታለች።
በሀገሪቱ አሁን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግበት አመታዊ አደን የሚካሄድ ሲሆን ይህም ለአካባቢው ማህበረሰብ የገቢ ምንጭ ሆኖታል።
ሂውማን ሶሳይቲ ኢንተርናሽናል በ2021 ያወጣው ሪፓርት እንደሚያመለክተው ከሆነ ጀርመን የአፍሪካ ዝሆን ትሮፊዎችን በመግዛት ቀዳሚ ሀገር ነች።
የጀርመን የአካባቢ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት ቦትስዋና ያጋጠማትን ችግር ለጀርመን አላነሳችም።
"የስነ ህይወታዊ ብዙየት እየጠፋ ባለበት ወቅት፣ ዝሆኖችን ማስገባት (ወደ ጀርመን) ዘላቂ እና ህጋዊ መሆኑን የማረጋገጥ ልዩ ኃላፊነት አለብን" ብለዋል ቃል አቀባይዋ።
አውስትራሊያ፣ ፈረንሳይ እና ቤልጀየም የዝሆን ትሮፊዎችን ንግድን ካገዱ ሀገራት መካከል ይገኙበታል።