እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይና ፖርቹጋል ለዋንጫው እንደሚፋለሙ ይጠበቃል
የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ከሰኔ 14 እስከ ሀምሌ 14 2024 በጀርመን አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
ተጠባቂው አህጉራዊ ውድድር በቀጣዩ ሳምንት አርብ አዘጋጇ ጀርመን ከስኮትላንድ ጋር በአሊያንዝ አሬና በሚያደርጉት የመክፈቻ ጨዋታ ይጀመራል።
24 ብሄራዊ ቡድኖች በስድስት ምድቦች የተመደቡ ሲሆን፥ አዘጋጇ ጀርመን፣ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ለዋንጫው ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል።
በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ለማለፍ በተደረጉት የማጣሪያ ጨዋታዎች ሁሉንም ግጥሚያዎች ያሸነፈችው የክርስቲያኖ ሮናልዶ ሀገርም ተጠባቂ ናት።
የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ በ10 የጀርመን ከተሞች የሚደረግ ሲሆን፥ መክፈቻው በአሊያንዝ አሬና የዋንጫ ጨዋታው ደግሞ በኦሎምፒያ ስታዲየም ይካሄዳል ተብሏል።
የውድድሩ ተሳታፊ ሀገራት ተጫዋቾቻቸውን ጠርተው ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ከየምድባቸው አንደኛና ሁለተኛ ሆነው የሚያጠናቅቁና አራት ምርጥ ሶስተኛ ብሄራዊ ቡድኖች ጥሎ ማለፉን ይቀላቀላሉ።
የጀርመኑ የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ድልድል ምን እንደሚመስል በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፦