በሰደድ እሳት ምክንያት ስፔንና ጀርመን ነዋሪዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ ትእዛዝ አስተላለፉ
600 መቶ የእሳት አደጋ ሠራተኞች ተሰማርተዋል
የእሳት አደጋው ስፔን ካሏት 17 ግዛቶች ውስጥ በ8ቱ መከሰቱ ተገልጿል
በአውሮፖ በተለይም በሰፔን የተከሰተው ሰደድ እሳት ከባድ ችግር ፈጥሯል። ስፔን በ40 አመት ውስጥ ለራሷ ከፍተኛ የተባለውን
ሙቀት ስታስመዘግብ ባለፈው ሳምንት በኢበሪያን ፔንዙላ የነበረው ሙቀት ከፍ ብሎ ነበር።
በጣም ከባድ ለተባለው ለዚህ እሳት አደጋ ምክንያት ነው የተባለው ሞቃታማ፣ደረቅና ንፋሳማ የሆነው አየር ንብረት ነው። ሲጂቲኤን እንደዘገበው የስፔን ጦር በሰሜን ስፔን የተከሰተውን እሳት ለመቆጣጠር ወደ ቦታው ተሰማርቷል።
በአርታዙ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀዋል፤ በሰራ ዲላ ኩሌብራ 25000 ሄክታር መሬት ተቃጥሏል።
በእንስሳት ሀብት በሚታወቀው አካባቢ ያለውን እሳት ለመቆጣጠር 600 የሚሆኑ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ተሰማርቸዋል ቱብሏል። 70 የሚደርሱ የወፍ ዝርያዎች እና የኢበሪያን ተኩላዎች ጉዳት ሳይደርስባቸው አይቀርም ተብሎ ተሰግቷል።
የእሳት አደጋጋ ሠራተኞቹና የአካባቢው ነዋሪዎች ከሳማዎችኖ ለማዳን እየተንቀሳቀሱ ሲሆን እሳቱ ከለገሪቱ 17 ግዛቶች በስምንቱ መከሰቱ ተዘግቧል።