ጀርመን በናዚ ዘመን ለተፈጸሙ ድርጊቶች የሚቀርቡ የካሳ ጥያቄዎችን እንዲያስቆምላት ተመድን ጠየቀች
ጣልያን በናዚ ዘመን ለተፈጸመ ክስተት የካሳ ጥያቄ እንዳታነሳ በጀርመን ተከሳለች
ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ቢሊዮን ዶላሮችን በጦርነቱ ለተጎዱ ሀገራት ካሳ መክፈሏንም ጀርመን ገልጻለች
ጀርመን በናዚ ዘመን ለተፈጸሙ ድርጊቶች የሚቀርቡ የካሳ ጥያቄዎችን እንዲያስቆምላት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፍርድ ቤትን ጠየቀች፡፡
ጀርመን እና ጣልያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአንድ ጎራ ሆነው ከተቀረው ዓለም ጋር ጦርነት ከፍተው በነአሜሪካ በሚመራው ቡድን መሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
ይሁንና ጣልያን በናዚ የአስተዳድር ዘመን ጊዜ ተፈጽመዋል ያለቻቸውን ድርጊቶች ወደ ፍርድ ቤቶች በመውሰድ ካሳ እንዲከፈላት ጠይቃለች፡፡ ሆኖም ይህ በጎረቤቷ በጀርመን አልተወደደላትም፡፡
ድርጊቱን የነቀፈችው ጀርመንም አስቁምልኝ ስትል ጉዳዩን የተመድ አካል ወደ ሆነው ዓለም አቀፉ ገላጋይ ፍርድ ቤት ወስዳለች እንደ ሮይተርስ ዘገባ፡፡
ጣልያን እና ጀርመን በናዚ ዘመን ለተፈጸሙ ድርጊቶች ካሳ ላለመጠየቅና በፍርድ ቤቶች ላለመካሰስ በፈረንጆቹ 2012 ላይ ተስማምተው ነበር፡፡
ይሁንና ከዚህ ስምምነት በኋላ ጣልያን 25 የናዚ ዘመን ካሳ ይከፈል የሚሉ ጉዳዮች በአገሯ ባሉ ፍርድ ቤቶች ላይ መቅረባቸውን ጀርመን ገልጻለች፡፡
የጣልያን ፍርድ ቤቶችም ከቀረቡለት ክሶች መካከል አብዛኞቹ ጀርመን ካሳ እንድትከፍል ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን በጣልያን ያሉ የጀርመን ኩባንያዎች የዚህ ውሳኔ ሰለባ መሆናቸውንም አክላለች፡፡
ጣሊያን በሩሲያ ላይ ካላት የነዳጅ ጥገኝነት ለመላቀቅ አፍሪካን እያማተረች ነው
በፈረንጆቹ 2008 ላይ በጣልያን ባሉ ሁለት የጀርመን ኩባንያዎች በፈረንጆቹ 1944 ላይ ለ203 ጣልያናዊያን መሞት ምክንያት ሆኗል በሚል ክስ ተመስርቶባቸው የ1 ሚሊዮን ዩሮ እንዲከፍሉ የጣልያን ፍርድ ቤት ከአንድ ወር በኋላ እንደሚወስን ይጠበቃል፡፡
ኩባንያዎቹ የካሳ ውሳኔውን ካልከፈሉ የድርጅቶቹ ሀብት ሊወረስ እንደሚችል የአገሪቱ ፋይናንስ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ጀርመን በበኩሏ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለደረሱ ውድመቶች ቢሊዮን ዩሮዎችን በጦርነቱ ለተጎዱ ሀገራት መክፈሏን ተናግራለች፡፡
ጀርመን የ300 ሺህ ሰራተኞች እጥረት እንደገጠማት ገለጸች
ጣልያን በ2012 ከጀርመን ጋር በናዚ የአስተዳድር ዘመን የተፈጠሩ የካሳ ጥያቄዎች በሀገሯ ባሉ ፍርድ ቤቶች እንዳይታዩ በሚል ያደረገቻቸውን ስምምነቶች እንድታከብርም ጠይቃለች፡፡
ጀርመን ዋና መቀመጫውን በኔዘርላንድ ሄግ ያደረገው ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ጣልያንን እንዲያስቆምላት ጠይቃለች፡፡