ጎግል የአፍሪካን የኢንተርኔት አገልግሎት ለማሳደግ 1 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ ማቀዱን አስታወቀ
ኢንቨስትምንቱ የአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን የሚያግዝ ነውም ተብሎለታል
ጎጉል ከሳፋሪኮም ጋር በመተባበር ዘመናዊ የአንድሮይድ ስልኮች ወደ አፍሪካ ገበያ ለማስገባት እንደሚሰራም አስታውቋል
ጎግል በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የአፍሪካን የኢንተርኔት አገልግሎት ለማሳደግና የአህጉሪቱን ስራ ፈጠራ መስክ ለማነቃቃት 1 ቢልዮን ዶላር ኢንቨስት እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡
በአፍሪካ ከፍተኛ የሆነ የኢንተርኔት(በይነ መረብ) ችግር በመኖሩ ከ1.3 ቢልዮን የአህጉሪቱ ህዝቦች አገልግሎቱን የሚያገኙት ሰዎች ቁጥር ከ1/3 ያነሰ እንደሆነ የዓለም ባንክ መረጃ ያመለክታል፡፡
በአፍሪካ ያለው የኢንተርኔት(በይነ መረብ) ተደራሽነት በሚፈለገው ደረጃ ባይሆንም ፤ 50 በመቶ የአህጉሪቱ ህዝቦች ከ18 ዓመት የዕድሜ ክልል በታች የሚገኙ በመሆናቸው የአፍሪካ አህጉር ዋና የገበያ ማእከል ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡
የጎግል ኃላፊው ሰንድራ ፒቻይ፡ ባለፉት ቅርብ ዓመታት“ግዙፍ እርምጃዎች”ቢታዩም “ እያንዳንዱ አፍሪካዊ በተመጣጣኝ ዋጋ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኝ”መስራት ይጠበቅብናል ማለታቸው የፈረንሳዩ የዜና ወኪል /ኤኤፍፒ/ዘግቧል፡፡
ኢንቨስትመንቱ የተሻሻለ ግንኙነትን እና ተደራሽነት እንዲኖር የሚያስችል እንዲሁም ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን የሚያግዝ ነውም ብሏል ሃለፊው፡፡
ገንዘቡ ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ ደቡብ አፍሪካ ፣ናሚቢያ ፣ ናይጄሪያ እና ሴንት ሄለናን ከአውሮፓ ጋር የሚያገናኘውን የኢኳኖ የከርሰ ምድር ገመድ ጨምሮ ለመሠረተ ልማቶች ግንባታዎች የሚውል እንደሆነም የተገለጸው፡፡
ስምምነቱ የ 10 ሚሊዮን ወጣት አፍሪካውያንን እና አነስተኛ የንግድ ሥራዎችን በዲጂታል ክህሎቶች ለማሠልጠን ከአራት ዓመት በፊት የጎግል የገባውን ቃል በበለጠ እንዲያሰፋ የሚያስችል ነውም ተብሎለታል፡፡
በአፍሪካ የጎጉል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ኒቲን ጋጅሪያ “የአፍሪካ ትልቅ ችግሮች ለመፍታት ከአፍሪካውያን የፈጠራ ባለሙያዎች ውጭ ማንም ሊመጣ አይችልም የሚል ጽኑ እምነት አለኝ” ሲሉ ተናግሯል፡፡
አሁን ላይ በዘመናዊ ስልኮች ምክንያት የኢንትርኔት (በይነመረብ) ተደራሽነት እንደተስተጓጎለ ይነሳል።
ጎጉል ፡ ከኬንያው የቢዝነስ አጋሩ ግዙፉ ሳፋሪኮም ጋር በመተባበር ዘመናዊ የአንድሮይድ ስልኮች በመያዝ ወደ አፍሪካ ገበያ ለማስገባት እንደሚሰራም አስታውቋል፡፡ ፕሮጀክቱ በቀጣይ እንደ ኤርቴል፣ኤምቲኤን፣ኦሬንጅ እና ቮዳኮም ከመሳሰሉ ኩባንያዎች ጋር እንደሚሰራበትም ተግለጸዋል፡፡