የሳተላይቶች አያት የምትባለው ኢአርኤስ-2 ሳተላይት ወደ ምድር እየተምዘገዘገች ነው ተባለ
ኢአርኤስ-2 ሳተላይት በ1990ዎቹ ነበር ወደ ህዋ እንድትመጥቅ የተደረገው
የአውሮፓ ጠፈር ሳይንስ ንብረት የሆችው ይህች ሳተላይት በእድሜ ምክንያት አገልግሎት አቋርጣለች
የሳተላይቶች ሁሉ አያት የምትባለው ኢአርኤስ-2 ሳተላይት ወደ ምድር እየተምዘገዘገች ነው ተባለ፡፡
የአውሮፓ ጠፈር ሳይንስ ኢንስቲትዩት በ1990ዎቹ ወደ ህዋ ያላካት ኢአርኤስ-2 ሳተላይት በእርጅና ምክንያት አገልግሎት ካቋረጠች ዓመታት አስቆጥራለች፡፡
የመሬት ላይ ምልከታዎችን ለማድረግ በሚል ወደ ህዋ የተላከችውይቺ ሳተላይት ለብዙ ዓመታት መረጃዎችን ስትልክ እንደቆየች ተገልጿል፡፡
ሳተላይቷ በተለይም የተለያዩ ውሳኔዎችን ለማስተላለፍ የሚረዱ ውሃማ ቦታዎች፣ የበረዶ ግግር፣ አደጋዎችን እና ሌሎች መረጃዎችን ለአውሮፓ ጠፈር ሳይንስ ኢንስቲትዩት ስትልክ ቆይታለችም ተብሏል፡፡
በ1995 የመጠቀችው ይቺ ሳተላይት በፈረንጆቹ 2011 ላይ በእርጅና ምክንያት አገልግሎት እንዳቋረጠችም ተገልጿል፡፡
በዛሬው ዕለት ወደ ምድር እየመጣች ነው የተባለችው ይቺ ሳተላይት 2 ቶን ክብደት እንደነበራት ሲገለጽ አብዛኛው አካሏ በጉዞ ላይ እያለች በሚፈጠር ሙቀት ራሷን ታቃጥላለች ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በጠፈር ላይ በርካታ ሳተላይት ያላቸው ሀገራት እነማን ናቸው?
በእሳት የማይወገደው የሳተላይቷ የተወሰኑት ቁሳቁሶች በምድራችን የትኛውም ቦታ ላይ ሊያርፍ እንደሚችል ተገልጿል፡፡
ይሁንና ሳተላይቷ ውሃማ አካባቢዎች ላይ እንደምታርፍ የተገመተ ሲሆን ምድርን ሊጎዳ የሚችል ኬሚካም ሆነ ሌላ ምርት እንደሌላት በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ሳተላይቷ ወደ ህዋ የተላከችበት ጊዜ መርዘሙ እና በተለይም ከ2 ሺህ ሚሊኒየም በኋላ በርካታ የተሸሻሉ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ ሳተላይቶች መላካቸውን ተከትሎ ኢአርኤስ-2 የሳተላይቶች ሁሉ አያት አስብሏታል፡፡