ኩባንያው አፕል እና ህዋዌን ለመፎካከር በሳተላይት የሚሰሩ ስልኮችን ለገበያ እንደሚያቀርብ አስታውቋል
ሳምሰንግ ኩባንያ በሳተላይት የሚሰራ ስልክ እንደሚሰራ ገለጸ።
የደቡብ ኮሪያው ስልምሰንግ ስልክ አፕል እና ህዋዌ የኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያዎችን ለመፎካከር አዲስ ስሪት ስልክ ለገበያ አቀርባለሁ ብሏል።
የኩባንያው ሲስተም ሀላፊ ፓርክ ያንግ ኢን እንዳሉት ከፈረንጆቹ 2024 ጀምሮ S24 የተሰኘ አዲስ ምርት ለገበያ እንደሚያቀርብ አስታውቀዋል።
ይህ አዲስ ስልክ ከዚህ በፊት አፕል እና ህዋዌ ኩባንያዎች የተሙረቱ እና ለገበያ የቀረቡ የሳተላይት ስልኮች ጋር ተመሳሳይ ይሆናል ተብሏል።
ይህ አዲስ ስልክ መደበኛ የስልክ ኔትወርኮችን ከመጠቀሙ ባለፈ የሳተላይቶችን ኮምንኬሽን ተጠቅሞ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል።
ይህን ስልክ የሚይዙ ደንበኞች በአደጋ ወቅት እና የስልክ ኔትወርክ አገልግሎት በሌሉባቸው አካባቢዎች መጠቀም ያስችላል ተብሏል።
የአምስተኛው ትውልድ ወይም 5G ኔትወርክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይገጠምለታል የተባለው ይህ ስልክ ደንበኞች ያለምንም ከልካይነት መልእክት መላክ እና መደዋወል እንደሚያስችልም ተገልጿል።
የአሜሪካው አፕል ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሳተላይት ኔትወርክን በመጠቀም መልዕክት መላክ የሚያስችል ስልክ ሰርቶ ነበር።
ይህ ስልክ መልዕክት መላክ እንጂ መቀበል የማያስችል የነበረ ሲሆን የቻይናው ህዋዌ ኩባንያ ደግሞ ቴክኖሎጂውን አሻሽሎ መደበኛ ኔትወርክ በሌለባቸውም ስፍራዎች መልእክት መላክ እና መቀበል የሚችል ስልክ ሰርቶ ነበር።
አሁን ደግሞ ሳምሰንግ ኩባንያ ከመልዕክት ባለፈ ስልክ መደዋወል፣ ፎቶ እና ተንቀሳቃሽ ምስል ሳይቀር መላላክ እና መቀበል የሚያስችል ስልክ በመስራት ላይ መሆኑን አስታውቋል።