ሩሲያ ከስፔስ የሚወነጨፍ "አስፈሪ" የጸረ-ሳተላይት መሳሪያ እየሰራች መሆኑን አሜሪካ ገለጸች
ቃል አቀባዩ ይህ መሳሪያ በአሁኑ ወቅት ወደ ስራ አለመግባቱን እና በመሬት ላይ ጉዳት እንደማያደርስ ተናግረዋል
የአሜሪካ ባለስልጣናት በመሳሪያው ቴክኖሎጂ ዙሪያ ያገኙትን መረጃ እየተነተኑ እና ከአጋሮች ጋር እየተመካከሩበት ነው ተብሏል
ሩሲያ ከስፔስ የሚወነጨፍ "አስፈሪ" የጸረ-ሳተላይት መሳሪያ እየሰራች መሆኑን አሜሪካ ገለጸች።
ኃይት ሀውስ በትናንትናው እለት ሩሲያ "አስፈሪ የሆነ" የጸረ-ሳተላይት መሳሪያ እስራች መሆኑን ይፋ አድርጓል።
የኃይት ሀውስ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ክርቢይ እንደገለጹት የአሜሪካ ደህንነት ባለስልጣናት ሩሲያ እንዲህ አይነት መሳሪያ የመስራት አቅም እንዳላት የሚያሳይ መረጃ አግኝተዋል።
ነገርግን ቃል አቀባዩ ይህ መሳሪያ በአሁኑ ወቅት ወደ ስራ እንዳልገባና እና በመሬት ላይ ጉዳት እንደማያደርስ ተናግረዋል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት በመሳሪያው ቴክኖሎጂ ዙሪያ ያገኙትን መረጃ እየተነተኑ እና ከአጋሮች ጋር እየተመካከሩበት ነው ተብሏል።
ክርቢይ "የሩሲያ መሳሪያውን የመጠቀም አቅም አስፈሪ ቢሆንም፣ አሁን ላይ መሳሪያው ወደ ስራ ስላልገባ የደቀነው ስጋት የለም" ብለዋል።
ክርቢይ "እያወራን ያለነው የሰው ልጆችን ለማጥቃት ጥቅም ላይ ስለሚውል ወይም በመሬት ላይ ውደመት ስለሚያስከትል መሳሪያ አይደለም" ሲሉ ቃል ተናግረዋል።
ኃይት ሀውስ ይህን መረጃ ይፋ ያደገው የሪፐብሊካኑ ሀውስ ኢንተሊጀንስ ኮሚቴ ኃላፊ የኦሀዮ ተወካይ የሆኑት ማይክ ተርነር ብሔራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል መረጃ መኖሩን እና የባይደን አስተዳደር እንዲመረምረው ካሳሰቡ በኋላ ነው።
ክርቢይ የሩሲን አቅም የመገምገም እና የመተንተን ሂደት ተርነር መግለጫ ባወጡበት ወቅት እየተካሄደ ነበር ብለዋል።
ክርቢይ አክለውም "የትኛው ጉዳይ ይተንተን እና ለህዝብ ይፋ ይሁን የሚለውን በጥንቃቄ ነው የምናየው" ሲሉ ተናግረዋል።
ሩሲያ ግን እንዲህ አይነት እቅድ እንደሌላት በመግለጽ የአሜሪካን ስጋት አጣጥላለች።