ቁጥሮች ስለዘንድሮው ሀጂ ጉዞ
ከ2 ሚሊየን በላይ ሙስሊሞች መካ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል
ሳኡዲ ከ32 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች እና 24 ሺህ አውቶብሶችን አዘጋጅታለች
ሙስሊሞች በአመት አንዴ ወደ መካ የሚያደርጉት ጉዞ ሀጂ ይሰኛል።
ቅድስቷን ከተማ መካ ለመርገጥ የሚጓዙትም ሃጃጆች ይባላሉ።
የሳኡዲ ሃጂና ኡምራ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ መሰረት በዘንድሮው የሃጂ ስነስርአት ከ2 ሚሊየን በላይ ሃጃጆች ይሳተፋሉ።
የመናውያንን ጨምሮ ከ160 ሀገራት ወደ መካ ሚና የሚገቡ እንግዶችን በተቀላጠፈ መልኩ ለማስተናገድ ዝግጅት መደረጉንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ቁጥሮች ስለዘንድሮው ሀጂ ጉዞ ምን ይላሉ፦