ጥምረቱ በቅርቡ የራሱን መገበያያ እና ተጨማሪ ሀገራት ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል
በፈረንጆቹ 2009 የተመሰረተው ብሪክስ የብራዚል ፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ ስብስብ ነው።
ዓለማችን በጥቂቶች ቁጥጥር ስር መዋል የለባትም የሚለው ይህ ጥምረት ተጨማሪ መገበያያ ገንዘብ ለዓለም እንደሚያስተዋውቅ ገልጿል።
የፊታችን ነሀሴ በደቡብ አፍሪካ ጉባኤውን እንደሚያደርግ የሚጠበቀው ብሪክስ አዳዲስ አባል ሀገራት ያቀረቡትን የእንቀላቀል ጥያቄ ምላሽ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ሳውዲ አረቢያ፣ አረብ ኢምሬትስ፣ ኢራን፣ ቱርክ፣ ግብጽ እና አልጀሪያ ብሪክስን ለመቀላቀል ጥያቄ ካቀረቡ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።