ሳኡዲ አረቢያ በሀጅ ተጓዠች ላይ ጥላ የነበረውን የቁጥርና የእድሜ ገደብ አነሳች
በኮሮና ወረርሽኝ ውስብስብ ፈተና ተደቅኖበት የነበረው የሀጂ ጉዞ ገደቡ ተነሳለት
የፈረንጆቹ 2022 የሀጅ ወቅት ከ2021 ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ በላይ የተጓዦ ብልጫ ነበረው
የሳኡዲ አረቢያ የመንግስት ብዙኸን መገናኛ የሀጅ እና ዑምራ ሚንስትርን ጠቅሶ እንደዘገበው መንግስት በአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት በሀጅ ተጓዦች ቁጥር ላይ ገደብ አይጥልም።
ሚንስቴሩ አክሎም በተጓዦች እድሜ ላይ ገደቦችም አይኖሩም ብሏል።
በፈረንጆቹ 2022 የሀጅ ወቅት የኡምራ መርሃ-ግብሮች በጠንካራ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ቢደረግም ኮሮና ወረርሽኝ ውስብስብ ፈተና ደቅኖ ነበር ተብሏል።
በሁለት የሀጅ ወቅቶች ስነ-ስርዓቱ ከሳኡዲ አረቢያ ዜጎችና ነዋሪዎች በመጡ ተምሳሌታዊ ቁጥሮች ተገድቦ ቆይቷል።
ሳኡዲ አረቢያ ጥብቅ የጤና ቁጥጥር በማድረግ ባለፈው ዓመት ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ምእመናን ከሀገሪቱ ውስጥ ሆነው ስርዓቱን እንዲፈጽሙ ፈቅዳለች።
የተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት የሀጅ የአምልኮ ስነ-ስርዓቱ ያለ ጤና እክል መጠናቀቁን ሮይተርስ ዘግቧል። ምንም እንኳን ከፈረንጆቹ 2021 የሀጅ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 14 በመቶ በላይ የተጓዦች ብልጫ ቢኖረውም።
60 ሽህ አማኞች ብቻ በ2021 በታሪካዊና ኃየማኖታዊው የሀጂ ጉዞ መታደም ችለዋል። ሮይተርስ እንደገበው ይህ ቁጥር በ2020 ከበረውና በጥቂት ሺህዎች ከተወሰነው ተጓዦች ገደቦችን ለላ የተደረገበት ነበር ተብሏል።