በ2035 ግማሹ የዓለም ህዝብ ከልክ ላለፈ ውፍረት ይጋለጣል ተባለ
በእስያ እና በአፍሪካ ከ4 ቢሊየን በላይ ሰዎች ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንደሚገጥማቸው አዲስ ጥናት አመላክቷል
አንዳንድ ሀገራት ከ55 በመቶ በላይ የሚሆነው ጎልማሳ ህዝባቸው ከመጠን ያለፈ ውፍረት ሊገጥመው ይችላል ተብሏል
በፈረንጆቹ 2035 ግማሹ የዓለም ህዝብ ከመጠን ላለፈ ውፍረት ተጋላጭ እንደሚሆን አዲስ ጥናት አመላከተ።
በአፍሪካ እና በእስያ ዝቅተኛ ወይም መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ውስጥ ወደ 4 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከመጠን በላይ ውፍረት እንደሚገጥማቸው ተጠቁሟል።
በዩናይትድ ኪንግደም የተመሰረተው ለትርፍ ያልተቋቋመ የአለም ኦበሲቲ ፌደሬሽን እንዳለው ከሆነ፤ የልጆች ከልክ ያለፈ ውፍረት መጠን በእጥፍ እንደሚጨምር ይጠብቃል።
እንደ ቡድኑ ገለጻ አንዳንድ ሀገራት ከ55 በመቶ በላይ የሚሆነው ጎልማሳ ህዝባቸው ከመጠን ያለፈ ውፍረት ሊገጥመዉ ይችላል።
በፈረንጆች 2019 ይፋ የሆነ መረጃ እንደሚያሳየው ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው ጎልማሶች ቁጥር ከሰባት ዓመት በፊት በጣም ዝቅተኛ ነበር።
ሀገራት ከፍተኛ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው ጎልማሶችን አላስመዘገቡም ነበር ተብሏል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለሞት ዋነኛ መንስኤ ሆኖ ተገኝቷል።
ቡድኑ በ2019 ጥናት ከመጠን በላይ ውፍረት በአንዳንድ ሀገራት እስከ 22 በመቶ ለሚሆኑት ሞት መንስኤ ነው ብሏል።
የዓለም ውፍረት ፌዴሬሽን የሳይንስ ዳይሬክተር ራኬል ጃክሰን-ሌች “ከፍተኛው ውፍረት መጨመር ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ ይታያል ብለዋል። ”