የሀይስኩል ተማሪዎች አጋቾችን ለመዋጋት ትጥቅ አነሱ
የጉሬሮ ግዛት አቃቤ ህግ ከያሁልፔምፖ መንደር አራት ሰዎች ከባለፈው የካቲት ወር ጀምሮ የደረሱበት አልታወቀም
በሜክሲኮ የገጠር መንደር እገታ መፈጸሙን ተከትሎ የሀይስኩል ተማሪዎች ትጥቅ አንስተዋል
የሀይስኩል ተማሪዎች አጋቾችን ለመዋጋት ትጥቅ አነሱ
በሜክሲኮ የገጠር መንደር እገታ መፈጸሙን ተከትሎ የሀይስኩል ተማሪዎች ትጥቅ አንስተዋል።
ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው አጋቾች ተቸግረናል ያሉ በገጠር ሜክሲኮ የሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ፖሊሶች እድሜያቸው ከ12 አመት የማይበልጥ ተማሪዎችን መመልመላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህ የሀገሪቱ በተወሰነ ክፍሏ እገታን ለመከላከል እየታገለች መሆኗን የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ሴት እና ወንድ ተማሪዎች በደቡብ ምዕራቧ ጉሬሮ ግዛት በምትገኘው አያሁልቴምፖ ተራራማ መንደር ከመሰማራታቸው በፊት ጠብመንጃ እና ዱላ ይዘው በአከባቢ ባለ የስፖርት ሜዳ ላይ ትርኢት አሳይተዋል።
"በዚህ ህገወጥነት ምክንያት መማር አልቻልንም" ሲል አንድ ምልምል ሚለኒዮ ለተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግራለች።
በሜክሲኮ ውስጥ ደሃ በምትባለው ጉሬሮ መንደር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ መጥቷል።
ባለፈው ጥር መጀመሪያ ላይ በእጽ አዘዋዋሪው ሚቾካና ተፈጽሟል በተባለ የድሮን ጥቃት 30 ሰዎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብት ተቋማት መግለጻቸው ይታወሳል።
የጉሬሮ ግዛት አቃቤ ህግ ከያሁልፔምፖ መንደር አራት ሰዎች ከባለፈው የካቲት ወር ጀምሮ የደረሱበት አልታወቀም።
የግዛቱ ባለስልጣን አካባቢውን ለማስጠበቅ ታዳጊ ተማሪዎቹ የበጎ ፈቃደኛ ፖሊሶችን እያጠናከሩ መሆኑን እና ወጣቶች ደግሞ የጠፉትን እየፈለጉ እንደሚገኙ ገልጿል።
በሜክሲኮ ከፍተኛ የዕጽ ማዘዋወር ወንጀል የሚፈጸም ሲሆን የሀገሪቱ ፖሊስም ይህን ለማስቆም በርካታ ዘመቻዎችን እያካሄደ ይገኛል።