የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ተከበረ
በበዓሉ ላይ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል
የኢሬቻ በዓል የምስጋና፣ የእርቅና የይቅርታ በዓል ነው
የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ተከበረ።
በአባገዳዎች ምርቃት በተጀመረው በዓል ላይ ሀደ ሲንቄዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ከማለዳው ጀምሮ ወደ ሆራ አርሰዴ የተመሙት የበዓሉ ታዳሚዎች በሀገር ባህል ልብስ ደምቀው ታይተዋል።
ኢሬቻ የምስጋናና የምልጃ በዓል መሆኑ ይነገራል።
በዚህ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ ምድርንና ሰማይን፣ ወንዝንና ባህርን፣ ቀንንና ሌሊትን፣ ብርሀንና ጨለማን፣ ሕይወትና ሞትን፣ ክረምትንና በጋን፣ ዝናብንና ሐሩርን፣ ዕጽዋትን፣ እንስሳትንና ሰውን ለፈጠረ፤ ሁሉን ነገር ማድረግ ለሚችል “ዋቃ” (አምላክ) ምስጋናና ክብር የሚያቀርብበት በዓል ነው።
የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ ለ5ኛ ጊዜ መከበሩ ይታወሳል።