ልዩልዩ
በወርቅና በውድ ግብዓቶች የሚሰራው የሳዑዲው ከዓባ ሽፋን ልብስ የመቀየር ስነ ስርዓት በፎቶ
የአንዱ የከዓባ ልብስ ዋጋም 17 ሚሊየን የሳዑዲ ሪያል አሊያም 4.53 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ያወጣል
ኪስዋ የከዓባ ልብስ 670 ኪሎ ግራም ጥቁር ሲልክ፣ 120 ኪሎ ግም ወርቅና 100 ኪሎ ግራም በብር ገመድ ነው የሚዘጋጀው
የሳዑዲ አረቢያ የሁለቱ ቅዱስ መስጊዶች አስተዳደር የጥገና እና የንብረት አስተዳደር ክፍል የከዓባ ግንብ ሽሃን ልብስ የመቀየር ስነ ስርዓት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቋል።
ከቁርዓን የተወሰዱ ጥቅሶች ያሉበት የከዓባው ልብስም እንዲወርድ በማድረግ በአዲሱ ልብስ የመቀየር ስራም እየተካሄደ ነው።
ኪስዋ በተባለ ኢንደስትሪ የሚዘጋጀው የከዓባው ልብስ 670 ኪሎ ግራም ጥቁር ሲልክ፣ 120 ኪሎ ግም ወርቅ እና 100 ኪሎ ግራም በብር ገመድ ነው የሚዘጋጀው።
የአንዱ የከዓባ ልብስ ዋጋም 17 ሚሊየን የሳዑዲ ሪያል አሊያም 4.53 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያወጣም ነው የተነገረው።
አሮጌው ኪስዋ በትናንሽ ቁርጥራጮች ተቆርጦ ለእስልምና እምነት ተከታዮች የሚሰጥ መሆኑም ተነግሯል።