ፖለቲካ
የሮኬት ጥቃት የደረሰባት እስራኤል ከፍተኛ የጋዛ አዛዥ ገደልኩ አለች
ከጋዛ የተተኮሰ ሮኬት በእስራኤል የሞት አደጋ ማድረሱን ተከትሎ እስራኤል በወሰደችው እርምጃ ከፍተኛ የጋዛ አዛዥ መግደሏን ገልጻለች
የፍልስጤም ታጣቂዎች አሁንም ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ከተሞች እየተኮሱ ናቸው
ከጋዛ የተተኮሰ ሮኬት በእስራኤል የሞት አደጋ ማድረሱን ተከትሎ እስራኤል በወሰደችው እርምጃ ከፍተኛ የጋዛ አዛዥ መግደሏን ገልጻለች።
እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በምትገኝ ካን ዩኑስ ከተማ ባካሄደችው የመኖሪያ ህንጻ የአየር ድብደባ ሶስት ፍልጤማውያን ሲገደሉ ሰባት የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል።
የሮኬት ፕሮግራም ኃላፊ የሆነው ሀሰን ጋሊ ከወንድሙ ጋር መገደሉን ሮይተርስ ዘግቧል።
ጋሊ ባለፈው ማክሰኞ እለት በተቀሰቀሰው ግጭት ከተገደሉ ታዋቂ ወታደራዊ አዛዦች መካከል አንዱ መሆኑም ተዘግቧል።
የእስራኤል ወታደራዊ አውሮኘላኖች በካን ዩኑስ የሚገኙ ሶስት መኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ አውድመዋል፤ እስራኤል ይህን ያደረገችው ነዋሪዎቹ እንዲወጡ ካስጠነቀቀች በኋላ ነው።
በትናንትናው እለት የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በእስራኤል ጥቃት ስድስት ህጻናትን ጨምሮ 25 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 70 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
የፍልስጤም ታጣቂዎች አሁንም ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ከተሞች እየተኮሱ ናቸው።