እስራኤላውያን የሀገሪቱ መንግስት የፍትህ ስርአቱን ለማሻሻል ያቀረቡትን ህግ በመቃወም ነው ጉዳና የወጡት
የእስራኤል ፓርላማ (ክኔሴት) እንዲያፀድቀው በኔታንያሁ የቀረበውን የፍትህ ስርአቱን ያሻሽላል የተባለው ህግ በመላ ሀገሪቱ ተቃውሞ ማስነሳቱን ተነግሯል።
እስራኤላውያን የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መንግስት የፍትህ ስርአቱን ለማሻሻል ያቀረቡትን ህግ በመቃወም ነው ጉዳና የወጡት።
ተቃዋሚች የፍትህ ስርአቱን ማሻሻል የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ጤና ይጎደል ሲሉ ሰግተዋል።
የእስራዔል ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጭሶችን እና ውሓ መጠቀሙ የተነገረ ሲሆን፤ አንአንድ ስፍራዎች ላይም ወደ ግጭት ግብቷል።