እስራኤል 400 የሚሆኑ ቤተ እስራኤላውያንን ከኢትዮጵያ ልትወስድ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙት “የፈላሻ ሙራ” (ቤተ እስራኤላውያን) ማህበረሰብ አባላት ወደ እስራኤል የሚሄዱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የእስራኤል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የማህበረሰቡ አባላት ተሳክቶላቸው መሄድ ከቻሉ በእስራኤል ካሉት ቤተሰቦቻቸው ጋር ይገናኛሉ፡፡
የእስራኤል መንግስት 400 የሚሆኑ የኢትዮጵያ ጀዊሽ ዘር ያላቸውን የማህበረሰብ አባላት በመውሰድ በስእራኤል ከሚገኙት የቤተሰብ አባሎቻቸው ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ ማቀዱን ቻናል 12ቴሌቪዥንን ጠቅሶ ዘታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል፡፡
እንደ ዘታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘገባ ከሆነ ባለስልጣናቱ ከኢትዮጵያ ምርጫ በፊት በየካቲት ወር መጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው ያለውን ሁኔታ ይታዘባሉም ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ፈላሻ ሙራ ማህበረሰብ ቀደምቶች ተገደው ወደ ክርስትና አምነት መቀየራቸውንም ዘገባው ያብራራል፡፡
አሁን ላይ በእስራኤል የሚኖሩ ቤተሰቦች ያሏቸው ወደ 800 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ፈላሻዎች በኢትዮጵያ እንደሚኖሩ ይገመታል፤ በእቅዱም ተከፋፍለው የነበሩ ከ60 ቤተሰቦችም ለመገናኘት ያስችላቸዋል፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኒታኒያሁ ወደም ቀደም ብለው በእስራኤል ቤተሰብ ያላቸውን 1000 የሚሆኑ የኢትዮጵያ ጀዊሾችን ለመውስድ ማቀዳቸው የሚታወስ ነው፤ በዚህ መሰረትም እስከአሁን 600 ሰዎች ወደ እስራኤል ተጉዘዋል፡፡
የኒታኒያሁ መንግስት ከአምስት አመት በፊት ሁሉንም በኢትዮጵያ የሚገኙ የጀዊሽ ማህበረሰብ አባላት ከጎንደርና ከአዲስ አባባ ለመውሰድ ወስኖ ነበር፡፡
አሁንላይ 140,000 የሚጠጉ የኢትዮጵያ ጀዊሾች በእስራኤል ይገኛሉ፡፡