የጣሊያኗ ላዚዮ ሮምን ጨምሮ በክልሉ ጋብቻቸውን ለሚፈጽሙ ጥንዶች 2 ሺህ ዩሮ እሰጣለሁ አለች
የላዚዮ ክልል የጋብቻ ቱሪዝምን ለማሳደግ በማሰብ ስጦታውን ማዘጋጀቱ ታውቋል
የውጭ ሀገራት ዜጎችም በላዚዮ ክልል የሰርግ ስነ ስርዓታቸውን ከፈጸሙ የገንዘብ ስጦታውን ያገኛሉ
በጣልያን ላዚዮ ክልል ሮም ከተማን ጨምሮ በክልሉ ውስጥ የሰርግ ስነ ስርዓታውን ለሚያካሂዱ ጥንዶች 2 ሺህ ዩሮ እንደሚሰጥ አስታወቀ።
በማዕከላዊ ጣሊያን የሚገኘው እና ሮም ከተማን በውስጡ የያዘው የላዚዮ ክልል የጋብቻ ቱሪዝምን ለማሳደግ በማሰብ ከዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱ ታውቋል።
የላዚዮ ክልል ላለፉት ሁለት ዓመታት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በቱሪዝም ዘርፍ ያጋጠመውን ከፍተኛ ኪሳራ ለማካካስ የስርግ ስነ ስርዓት ስጦታውን ማዘጋጀቱም ተነግሯል።
ስጦታውን የሚያገኙ ጥንዶችም ጣሊያናውያን እና በከልሉ ውስጥ የሰርግ ስነ ስርዓታቸውን የሚፈጸሙ የውጭ ሀገራት ዜጎች ናቸው የተባለ ሲሆን፤ የያዝነው 2022 እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሰርጋቸውን የሚፈፅሙ ጥንዶች የገንዘብ ስጦታውን ያገኛሉ ተብሏል።
ሙሽሮች ለሰርግ ስነ ስርዓታቸው ላይ ለፀጉር ስራ እና ፍሸና፣ ለካሜራ እና ለሌሎች ጉዳዮች ያወጧው ወጪዎች እንደሚለስላቸው መጠየቅ እንደሚችሉም ታውቋል።
የክልሉ ባለስልጣናት በኮቪድ 19 ሳቢያ የተጎዳውን የጋብቻ ቱሪዝም ለማነቃቃት እና የጋበቻ ስና ስነስርዓቶችን የሚያከናውኑ ተቋማትን ለመደግፍም 10 ሚሊየን ዩሮ መመደባቸው ታውቋል።
ላዚዮ ከዚህ ቀደም ከጣሊያን እና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተውጣጡ በአመት ከ15 ሺህ የሚበልጡ የሰርግ ስነ ስርዓቶችን ታስተናግድ እንደነበረ ይነገራል።
የኮቪድ 19 ወረርሽን በፈጠረው ጫና ሳቢያ ላለፉት ሁለት ዓመታት ግን ይህ ቁጥር መቀነሱ የተነገረ ሲሆን፤ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2021 9 ሽህ የሰርግ ስነ ስርአቶችን እንዳስተናገደችም ታውቋል።