የ“H” የፊደል ቅርጽ ያለው 2 ጋቢናዎችን በአንድ ላይ ያጣመረው ክንፉ 116 ሜትር ርዝመት አለው
የዓለማችን ግዙፉ የመንገደኞች አውሮፕላን በሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ በአሜሪካዋ ደቡብ ካሊፎርኒያ በረሃ አካባቢ ላይ ለ4ኛ ጊዜ የተሳካ የበረራ ሙከራ ማድረጉ ታውቋል።
116 ሜትር ርዝመት ባለው ክክፉ ምክንያት የዓለማችን ግዙፉ እንደሆን የተነገረለት አውሮፓኑ ለ1 ሰዓት ከ43 ደቂቃ ገደማ ከመሬት በ15 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ መብረር መቻሉ ታውቋል።
የ “H” የፊደል ቅርጽ ያለው አውሮፕላኑ በአየር ላይ በነበረው ቆይታ በሰዓት ከ286 ኪሎ ሜትር በላይ መጋዟ መቻሉ የተነገረ ሲሆን፤ የሙከራ ስራው ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ ግን በሰዓት እስከ 850 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላል ነው የተባለው።
አውሮፓልኑ የበረራ ሙከራውን በሚያደርግበት ጊዜ ሶስት ሰዎች ተሳፍረው ነበር የተባለ ሲሆን፤ እንዚህም ሁለት አብራሪዎች እና አንድ የበረራ ኢንጂነር መሆኑ ተነግሯል።
አውሮፕለኑን እየሰራ ያለው ስታርቶላውንች ኩባንያ እንዳስታወቀው አውሮፕላኑ እስከ ከጣዩ የፈረንጆቹ 2023 አጋማሽ ድረስ ሙሉ በሙሉ የሙከራ በረራውን አጠናቆ ወደ ስራ ይገባል።
የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ዛቻሪ ክሬቮር፤ አሁን የተካሄደው የበረራ ሙከራ ላይ የተገኘው ስኬት አውሮፕላኑ ወደ ስራ ለመግባት እየተቃረበ መሆኑን ያመላክታል ብለዋል።