የተራቆተ ተራራ ላይ ከ25 ሚሊየን በላይ ዛፎችን በመትከል ወደ ደንነት የቀየሩት ቱርካዊ ግለሰብ
የሲኖፕ ከተማን ወደ አረንጓዴነት የቀየሩት ሂክመት ካያ ከበርካቶች አድናቆት እየጎረፈላቸው ነው
ሂክመት ካያ የተባሉት ግለሰቡ በተራራው ላይ ለ24 ዓመታት የዛፍ ችግኞችን ተክለዋል
የተራቆተ ተራራማ አካባቢን ወደ ጥቅጥቅ ደህንነት የቀየሩት ቱርካዊው ሂክመት ካያ ከበርካቶች አድናቆት እየጎረፈላቸው ነው።
ግለሰቡ በቱርኳ ሲኖፕ ከተማ የሚገኝ የተራቆተ ተራራማ አካባቢን ነው ወደ ውብ እና ጥቅጥቀቅ ደንነት የቀየሩት።
ደን ልማት ባለሙያ የሆኑት ጡረተኛው ሂክመት ካያ ላለፉት 24 ዓመታት ሲኖፕ ከተማ የሚገኝ የተራቆተ ተራራማ አካባቢ ላይ ደን መትከላቸው ይነገራል።
የቦያባት የደን ልማት ድርጅት ባለሙያ የነበሩት ሂክመት ካያ በስራቸው ላይ እያሉ ሲኖፕ ከተማ የሚገኝ የተራቆተ ተራራማ አካባቢን ደን ማልበስ እንደጀመሩ ይነገራል።
በፈረንጆቹ 2002 ከስታቸው በጡረታ የተሰናበቱት ሂክመት ካያ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥም 25 ሚሊየን የዛፍ ችግኞችን መትከላቸው ተነግሯል።
ሂክመት ካያ ባለፉት 24 ዓመታት ለሰሩት ስራ እውቅና ለመስጠት በቅርቡ ወደ ሲኖፕ ከተማ መጠራታቸውም ታውቋል።
ግለሰቡ ተራራማው አካባቢ ከ24 ዓመታት በፊት የሚያሳየውን ምስል እና አካባቢው አሁን ላይ ምን እንደሚመስል ለማሳየት የተነሱት ፎቶግራፍ በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል።
ሂክመት ካያ “ይህንን የተራቆተ አካባቢ ወደ ደንነት መቀየር በመቻሌ በጣም ኩራት ይሰማኛል፤ ከዓመታት በኋላ አካባቢው እንደዚህ በደን ተሞሎቶ ስመለከትም ጥሩ ስሜት አእንዲሰማኝ አድርጓል” ብለዋል።
“ሁሉም ሰው ደኖችን እንደ ራሱ በእንክብካቤ ሊይዝ ይገባል” ሲሉም ተናግረዋል።