"just setting up my twttr" የሚለው የጃክ ዶርሴ የመጀመሪያ ትዊት ነው
የትዊተር መስራች ጃክ ዶርሴ የመጀመሪያ ትዊት በ2 ነጥብ 9 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማሌዢያዊ ባለሃብት ተሸጠ።
"just setting up my twttr" የሚለው የጃክ ዶርሴ የመጀመሪያ ትዊት በአውሮፓውያኑ መጋቢት 12 2006 ትዊት መደረጉን ቢቢሲ ዘግቧል።
ታዲያ የትዊተር መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ጃክ ዶርሴ ይህንን የመጀመሪያ ትዊቱን ለጨረታ በማቅረቡ ነው በ2 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ሊሸጥ የቻለው።
ጃክ ዶርሴ ከትዊቱ የሚገኘውን ገቢ ለበጎ አድራጎት ተግባር ለማዋል ለጨረታ እንዳቀረበውም ተነግሯል።
ማሌዢያዊው ባለሀብት ሲና ኤስታቫቲ የጃክ ዶርሴን ትዊት የኢንተርኔት መገበያያ በሆነው ክሪፕቶከረንሲ አማካኝነተ መግዛታቸውም ታውቋል።
በዚህም መሰረት ጃክ ዶርሴ ከሽያጩ 95 በመቶውን የሚያገኝ ሲሆን፤ ጨረታውን በኢንተርኔት አማካኝት ያካሄደው ሴንት የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ደግሞ 5 በመቶውን የሚወስድ ይሆናል።
ማሌዢያዊው ባለሀብት ሲና ኤስታቫቲ ጨረታውን በማሸነፍ የትዊቱ ባለቤት ቢሆኑም፤ ትዊቱ ግን ለህዝብ ይፋ በሆነ መልኩ ትዊተር ላይ ይቀመጣል ተብሏል።