ትራምፕ “እኛ አያሸነፍን ነው፤ እነሱ ግን ምርጫውን ለመስረቅ እየሞከሩ ነው…”ብለው ነበር የጻፉት
ትራምፕ “እኛ አያሸነፍን ነው፤ እነሱ ግን ምርጫውን ለመስረቅ እየሞከሩ ነው…”ብለው ነበር የጻፉት
ትዊተር ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው የጻፉት መልእክት አከራካሪ ወይም የምርጫውን ሁኔታ የሚያሳሳት በመሆኑ እንዲታገድ መደረጉን አስታውቋል፡፡
በአሜሪካ እየተካሄደ ባለው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ በሪፐብሊካን በመወከል ስልጣን ላይ ያሉት ዶናልድ ትራምፕ፣ በዲሞክራቶችን በመወከል ደግሞ ጆ ባይደን እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
እስካጀሁን ባለው ውጤት ጆ ባይደን በ225 ወካይ ድምጽ በመመብራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ትራምፕ በ213 ድምጽ ይከተላሉ፡፡ ይሁንና የምርጫንና ውጤት የሚወስኑ ዋና ዋና ግዛቶች ውጤት እስካሁን ተጠቃሎ ይፋ አልተደረገም፡፡
“እኛ አያሸነፍን ነው፤ እነሱ ግን ምርጫውን ለመስረቅ እየሞከሩ ነው፡፡ እኛ ይሄን እንዲያደርጉ አንፈቅድም፡፡ ምርጫ ጣቢያዎች ከተዘጉ በኋላ ድምጽ መሰጠት የለበትም” የሚል መልእክት ነበር ያስተላለፉት፡፡
ፕሬዘዳንት ትራምፕ ምርጫውን የሚሸንፍ ከሆኑ ለቀጣይ አራት አመታት የመምራት እድል ያገኛል፡፡