አቶ ጃዋር መሐመድ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) አባል ሆነ
የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተርና አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የሚመሩትን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ)ን መቀላቀሉ ተገለጸ፡፡
የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለአል አይን እንደገለጹት አቶ ጃዋር መሐመድ ከዚህ ቀደም የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮን) ይደግፍ ነበር ከዚህ በኋላም የፓርቲያችን አባል ነው ብለዋል፡፡
ቀደም ሲል ፖለቲካ ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው የገለጸው ጃዋር በፊትም ቢሆን ኦፌኮን ከውጭ ሆኖ ይደግፍ ነበር ብለዋል ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና።
አቶ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ በምርጫ እንደሚወዳደር የገለጸ ቢሆንም የትኛውን ፓርቲ እንደሚቀላቀል ይፋ አላደርገመ ነበር፡፡
የዜግነት ጉዳይን በሚመለከት እንዴት ልታደርጉ ነው በሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ፕሮፌሰር መረራ እኛ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ነው የምናውቀው ብለዋል፡፡
አክቲቪስት ጃዋር ከሰሞኑ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ባሉበት በኦፌኮ ጽህፈት ቤት ጉብኝት ማድረጉ ተሰምቷል።