ኬንያና ጅቡቲ የተመድን መቀመጫ ለማግኘት በ2ኛ ዙር እየተወዳደሩ ነው
በመጀመሪያ ዙር በተካሄደው ውድድር ኬንያ 113 ድምጽ ስታገኝ ጅቡቲ በአንጻሩ 78 ድምጽ አግኝታለች
ኬንያና ጅቡቲ የተመድን ጸጥታ ምክርቤት ቋሚ ያልሆነ መቀመጫ ለማግኘት እየተወዳደሩ ነው
ኬንያና ጅቡቲ የተመድን ጸጥታ ምክርቤት ቋሚ ያልሆነ መቀመጫ ለማግኘት እየተወዳደሩ ነው
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) በዛሬው እለት አንዳስታወቀው ኬንያና ጅቡቲ በተመድ የጸጥታው ምክርቤት ቋሚ ያልሆነ መቀመጫ ለማግኘት የሚያደርጉትን የሁለተኛ ዙር የምርጫ ውድድር ያካሂዳል፡፡
በመጀመሪያ ዙር በትናንትናው እለት በተካሄደው ውድድር ኬንያ 113 ድምጽ ስታገኝ ጅቡቲ በአንጻሩ 78 ድምጽ ማግኘቷን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ ነገርግን በተመድ ህግ መሰራት አሸናፊ ለመሆን 2/3 የተመድ አባል ሀገራትን ድምጽ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡
ኬንያ ከፍተኛ ድጋፍ ከአፍሪካ ህብረት እንዳላት ገልጻለች፡፡ ኬንያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር ጠንካራ ግንኙነት አላት ያሉት የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የኬንያ የዲሞክራሲና ከብዙ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት አውስተዋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ ኬንያ የምታሸንፍ ከሆነ የአፍሪካን አጀንዳ ወደ ፊት እንዲመጣና አለምአቀፍ ወንድማማችነት እንዲጎለብት እንደምትሰራ ተናግረዋል፡፡
ጅቡቲ በአንጻሩ ከእስላማዊ ድርጅቶች፣ ከአረብ ሊግና ከፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች ህብረት ድጋፍ እያገኘች ነው፡፡ ጅቡቲ በአፍሪካ ያለችበትን ወሳኝ የሆነ ቦታና ለብዙ ሀገራት ወታደራዊ ጦር ሰፈር መቀመጫ መሆኗን አንደምክንት በማቅለብ ቋሚ ያልሆነ የተመድ መቀመጫ ማግኘት አንደሚገባት እየገለጸች ትገኛለች፡፡
አሸናፊው ሀገር ከዚህ በፊት በተመድ የጸጥታው ምክርቤት ቋሚ ያልሆነ መቀመጫ ካላቸው ቱኒዚያና ኒጀር ጋር ይቀላቀላል፡፡