10 ከታዳሽ ምንጭ ከፍተኛ ሃይል የሚያገኙ ሀገራት
ከንፋስ ሃይል ብቻ 400 ጊጋ ዋት ሃይል የምታገኘው ቻይና ቀዳሚውን ደረጃ ይዛለች
በ2027 ከታዳሽ ሃይል የሚገኘው ኤሌክትሪክ በ2 ሺህ 400 ጊጋ ዋት እንደሚጨምር ይጠበቃል
በርካታ ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀትን ከ2020 እስከ 2030 በሁለት ሶስተኛ ይቀንሳሉ ተብለው የሚጠበቁ የታዳሽ ሃይል ልማት ፕሮጀክቶችን ጅምረዋል።
እንደ ቻይና ያሉ ግዙፍ ሀገራት የጀመሯቸው ፕሮጀክቶችም በቀጣይ ሁለት አመታት የአለምን የታዳሽ ሃይል ምንጭ በ55 በመቶ እንደሚያሳድጉ ነው የሚጠበቀው።
አለም ከታዳሽ ምንጮች የምታገኘው የኤሌክትሪክ ሃይል በ2027 በ2 ሺህ 400 ጊጋ ዋት እንደሚጨምርም የአለም ኢነርጂ ተቋም (አይኢኤ) መረጃ ያሳያል።
በቀጣይ አምስት አመታት ሀገራት ከባቢ አየርን ከማይበክሉ የሃይል ምንጮች የሚያገኙት ኤሌክትሪክ በ75 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል ብሏል ተቋሙ።
ከንፋስ፣ ጸሃይ እና የውሃ ግድብ ከፍተኛ ሃይል(በጊጋ ዋት) የሚያገኙ 10 ሀገራትን ይመልከቱ፦