ሊዮኔል ሜሲ ኢንተር ማያሚን የዋንጫ ባለቤት ለማድረግ መቃረቡን ተከትሎ በምርጫዬ 'ደስተኛ ነኝ' አለ
ሜሲ በሀምሌ ወር ለክለቡ ከፈረመ በኋላ ባደረጋቸው 6 ጨዋታዎች 9 ጎሎችን አስቆጥሯል
ኢንተር ማያሚ ለሊግ ዋንጫ ቅዳሜ ይጫወታል
አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ 'የሜጀር ሊግ እግር ኳስ' ዋንጫን ክለቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለቤት ለመሆን የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ካሸነፈ በኋላ ለኢንተር ማያሚ በመፈረሙ "በጣም ደስተኛ ነኝ" ብሏል።
ሜሲ በሀምሌ ወር ለክለቡ ከፈረመ በኋላ ባደረጋቸው 6 ጨዋታዎች 9 ጎሎችን አስቆጥሯል።
ይህም በክለቡ የምንግዜም ከፍተኛ የጎል አስቆጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ በሦስተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አድርጎታል።
ኢንተር ሚያሚ በግማሽ ፍጻሜ ፊሎደልፊያ ዩኒየንን 4 ለ 1 አሸንፏል። ሜሲ በጨዋታው አንድ ጎል አስቆጥሯል።
ድሉ ክለቡ ቅዳሜ ናሽቪል ቴነሲ ላይ ናሽቪል ኤስ ሲን ለፍጻሜ ጨዋታ ያገናኘ ሲሆን፤ በአራት የውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ ጨዋታውን እንዲያሸንፍ እድል አግኝቷል።
ሜሲ ህይወትን በአሜሪካ ገና እያስተካከለ መሆኑን ተናግሮ፤ ሳዑዲ አረቢያ ወይም ሌላ ቦታ ለመዛወር ነበረው ስለተባለው ፍላጎት ለኢንተር ማያሚ ለመፈረሙ ባደረገው ውሳኔ ደስተኛነቱን ገልጿል።
"ወደዚህ የመጣሁት ለመጫወት እና በእግር ኳስ ለመደሰት ነው። ይህም ህይወቴን በሙሉ የምወደው ነው። እናም ይህንን ቦታ የመረጥኩት በእነዚህ ነገሮች ምክንያት ነው" ሲል ሜሲ ለጋዜጠኞች ተናግሯል።
የ36 ዓመቱ ተጨዋች በተለይ ከፍሎሪዳ የአየር ሁኔታ ጋር ለመላመድ ጊዜ እንደሚጠይቀው ተናግሯል።