በውጭው ዓለም ዝነኛ የሆኑ በኢትዮጵያ ግን ብዙ ያልተለመዱ የማህበራዊ ትስስር ኩባንያዎችን እናስተዋውቅዎ
ኪውኪው፣ ፒንትረስት፣ ሬዲት፣ዊቻት ተምብለር እና ሌሎችም የማህበራዊ ትስስር ኩባንያዎች ብዙ ተከታዮች አሏቸው
እነዚህ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በየወሩ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች እንዳላቸው ተገልጿል
በውጭው ዓለም ዝነኛ የሆኑ በኢትዮጵያ ግን ብዙ ያልተለመዱ የማህበራዊ ትስስር ኩባንያዎችን እናስተዋውቅዎ
ያለንበት ዘመን የሰዎች ግንኙነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቀላል የሆነበት ወቅት ሲሆን መረጃዎች ከአንዱ ጫፍ ወደ ሌላኛው በፍጥነት እየተዳረሱ ናቸው፡፡
የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ይህ እንዲሆን የላቀ አበርክቶ ያላቸው ሲሆን የተራራቁ ሰዎች እነዚህን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የዕለት ከዕለት ግንኙነቶቻቸውን እያጎለበቱ ይገኛሉ፡፡
ሁሉም ቴክኖሎጂዎች አሳራራቸው፣ዓላማቸው እና ስርዓታቸው አንድ ባይሆንም በውድድር ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው ለሰዎች ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥረዋል፡፡
እንደ ፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ቴሌግራም፣ ዋትስአፕ እና መሰል የማህበራዊ ትስስር ገጾች በኢትዮጵያ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሏቸው ሲሆን ኢትዮጵያዊያን በጥቂቱ አልያም ሙሉ ለሙሉ የማያውቋቸው የትስስር ገጾች እንዳሉ ይታመናል፡፡
በዓለማችን 100 ሚሊዮን እና ከዛ በላይ ተከታይ ያላቸው ከ30 በላይ የማህበራዊ ትስስር ኩባንያዎች ያሉ ሲሆን የተወሰኑትን እና በኢትዮጵያዊያን ብዙ የማይታወቁ የማህበራዊ ትስስር ኩባንያዎችን እንደሚከተለው አዘጋጅተንላችኋል፡፡
ኩዌሹ የተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ኩባንያ በመላው ዓለም ከ670 ሚሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡
መሰረቱን ቻይና ያደረገው ይህ ኩባንያ ቲክቶክ ከተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ኩባንያ ጋር ተቀራራቢ የሆነ አገልግሎት በመስጠት ይታወቃል፡፡
ሌላኛው በኢትዮጵያ ብዙ ያልታወቀ የማህበራዊ ትስስር ኩባንያ ፒንትረስት የሚባል ሲሆን በየወሩ ከ465 ሚሊዮን በላይ ንቁ ተጠቃሚዎች አሉት ተብሏል፡፡
ኢንተርኔት በመዝጋት ከፍተኛ ገቢ ያጡ የዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ከ14 ዓመት በፊት በአሜሪካ የተቋቋመው ፒንትረስት በተለይም ምስሎችን ለማስቀመጥ እንዲውል ታስቦ የተሰራ ቢሆንም ቀስ በቀስ ግን አነቃቂ እና በሳል ጽሁፎችን ከምስሎች ጋር ለማሰራጨት ጥቅም ላይ እየዋለ መጥቷል፡፡
ሬዲት የተሰኘው እና ወርሃዊ ከ430 ሚሊዮን በላይ ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን በተለይም የቡድን ውይይቶች ላይ ለመሳተፍ እና ጥያቄዎችን ለመመለስ ተመራጭ የማህበራዊ ትስስር አማራጭ ነው፡፡
ታዋቂ ሰዎች ይህንን የማህበራዊ ትስስር አማራጭ በመጠቀም የሚታወቁ ሲሆን ጠይቁኝ ወይም አስክ ሚ ኤኒ ቲንግ የሚል ታዋቂ አቀራረብ ያለው ሲሆን ተከታዮች የፈለጉትን እና እንዲመለስ የሚፈልጉትን ሀሳብ ታዋቂ ሰዎችን ይጠይቁበታል፡፡
ሌላኛው የአሜሪካ የማህበራዊ ትስስር ኩባንያ ዲስኮርድ የሚሰኝ ሲሆን ከ150 ሚሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎችን በመያዝ የጽሁፍ፣ ድምጽ፣ ፎቶ እና ቪዲዮ መልዕክቶችን መለዋወጥ ያስችላል፡፡
ተምብለር የተሰኘው ሌላኛው የማህበራዊ ትስስር ኩባንያ ልክ እንደ ፌስቡክ ተመሳሳይ አገልግሎት መስጠት የሚችል ሲሆን በሰሜን አሜሪካ ሀገራት ብዙ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡