ኢኮኖሚ
ኢንተርኔት በመዝጋት ከፍተኛ ገቢ ያጡ የዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ሩሲያ 113 ሚሊዮን ዜጎቿን ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ በማድረግ ቀዳሚዋ ሀገር ተብላለች
ኢትዮጵያም ሌላኛዋ ኢንተርኔት ለረጅም ጊዜ የዘጋች ሀገር ስትሆን 1.6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማጣቷ ተገልጿል
ኢንተርኔት በመዝጋት ከፍተኛ ገቢ ያጡ የዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
በፈረንጆቹ 2023 ላይ 25 የዓለማችን ሀገራት ኢንተርኔት አቋርጠዋል የተባለ ሲሆን በኢትዮጵያ ሁሉም ማሕበራዊ የትስስር ገጾች መታገዳቸው ተገልጿል፡፡
ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በመከታተል እና ሪፖርቶችን በማውጣት የሚታወቀው ኔት ብሎክስ የ2023 ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ ተቋም ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ከኢንተርኔት በመዝጋት ገቢ ካጡ ሀገራት መካከል ከሩሲያ በመቀጠል ከፍተኛ ገቢ ያጣች ሀገር ተብላለች፡፡
ሩሲያ 113 ሚሊዮን ዜጎቿን ከኢንተርኔት ውጪ በማድረጓ አራት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ስታጣ ኢትዮጵያ ደግሞ 30 ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ ተደርገዋል፡፡
ሆን ተብሎ በመንግስት እንደተወሰደ የተገለጸው ይህ ኢንተርኔት ማቋረጥ ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አሳጥቷታል ተብሏል፡፡