ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በኢንተርኔት መዘጋት ከ5 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በማጣት ቀዳሚዎቹ ተጎጂዎች ናቸው
በ2023 በ25 ሀገራት በመንግስታት ውሳኔ ለ79 ሺህ 238 ስአታት ኢንተርኔት እንዲቋረጥ ተደርጓል።
በዚህም 747 ሚሊየን ሰዎች ተጠቂ መሆናቸውንና ከ9 ቢሊየን ዶላር በላይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት መድረሱን ነው የኢንተርኔት መቋረጥን የሚከታተለው ቶፕቴንቪፒኤን ድረገጽ ያስነበበው።
በአፍሪካም በተለይ ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት ከ84 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ሰዎችን የንግድ፣ የስራ እና የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ያወኩ የኢንተርኔት መቆራረጦች ተከስተዋል።
በ2023 ኢንተርኔትን በመዝጋት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ሩሲያ ናት፤ ሞስኮ ኢንተርኔት በማቋረጧ ምክንያት ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ አጥታለች። ኢትዮጵያ እና ኢራን ይከተላሉ።
ባለፈው አመት በተደጋጋሚ ኢንተርኔት በመዝጋት ቀዳሚዋ ሀገር ኢራን ናት፤ ከፈተናዎች ጋር በተያያዙና በሌሎች ምክንያቶች 66 ጊዜ ኢንተርኔት ዘግታለች።
በ2023 ኢንተርኔት በመዘጋት ዋጋ የከፈሉ 10 ሀገራትን ይመልከቱ፦