ደቡብ አፍሪካ ፍጹም ቅጣት ምቱን ያገኘችው ጨዋታው ከተጀመረ በ18ኛው ደቂቃ ሲሆን ታው ኳሷን ከኢላማ ውጭ አድርጓታል
ማሊ ደቡብ አፍሪካን አሸነፈች።
ትናንት ምሽት በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ማሊ ሳትጠበቅ ደቡብ አፍሪካን 2-0 ድል አድርጋለች።
ማሊ በስድስት ደቂቃ ልዩነት ባስቆጠረቻቸው ሁለት ግቦች ማሸነፏን ሮይተርስ ዘግቧል።
የደቡብ አፍሪካ ፐርሲ ታው ፍጽም ቅጣት ምት ከሳተ በኋላ የማሊው አምበል ሀማሪ ትራዎሬ ጨዋታው ከተጀመረ ከአንድ ሰአት በኋላ የመጀመሪያዋን ግብ ማስቆጠር ችሏል።
የመጀመሪያዋ ጎል ከገባች ከስድስት ደቂቃ በኋላ ላሳይን ሲንያኮ ለማሊ ሁለተኛዋን ግብ አስቆጥሯል።
ላሲን ሲንያኮ ሁለተኛዋን ጎል ማስቆጠር የቻለው ሁለት ተከላካዮችን በማለፍ ነበር።
ደቡብ አፍሪካ ፍጹም ቅጣት ምቱን ያገኘችው ጨዋታው ከተጀመረ በ18ኛው ደቂቃ ሲሆን ታው ኳሷን ከኢላማ ውጭ አድርጓታል።
ደቡብ አፍሪካ በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ጫና ፈጥራ መጫወት የቻለች ቢሆንም በሁለተኛው አጋማሽ በተፈጠረው የተከላካይ ክፍተት ተሸንፍላች።
ከእረፍት በኋላ ማሊም ሁለት ምርጥ የሚባሉ የጎል እድሎችን አግኝታ የነበረ ቢሆንም ሳትጠቀምበት ቀርታለች።