ኮትዲቫር እያስተናገደችው ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ የመክፈቻ ወድድር ጊኒ ቢሳውን 2-0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች
ኮትዲቮር የአፍሪካ ዋንጫን የመክፈቻ ወድድር አሸነፈች።
ኮትዲቫር እያስተናገደችው ባለው የአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ ወድድር ጊኒ ቢሳውን 2-0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
የኮትዲቮር ቡድን ጠንካራ የሚባል ጨዋታ ባያታሳይም፣ በደስታ ሰሜት የተሞሉት ደጋፊዎች መጠጥ ቤቶችን እና ጎዳናዎችን ማጨናነቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ደጋፊዎቹ በሰልፍ በመሆን ከአልሀሰኔ ኳታራ ኦሎምፒክ ስቴድየም ተጨዋቾቹን በሰልፍ በማጀብ ሸኝተዋል።
ግቦቹ በሁለቱም የጨዋታ አጋማሾች የተመዘገቡ ሲሆን ግቦችን ያስቆጠሩት ደግሞ ሴኮ ፎፋና እና ፊሊፕ ክራሶ ናቸው።
ኮትድቮር ብታሸነፍም ያሳችው ብቃት ግን አስተችቷታል።
"ዋናው ነገር ማሸነፋችን ነው። ስቴዲየም ሙሉ ተመልካች ባለበት የመክፈቻ ጨዋታ መጫወት ቀላል አይደለም" ሲሉ የኮትዲቮር አስልጣኝ ጂን ሉይስ ጋሴት ተናግረዋል።
"በስነልቦና ከባድ ነበር፤ ነገርግን የምንችለውን አድርገናል። በጣም ጥሩ ጅምር አለን፤ አጠቃላይ የቡድኑ አቅም ግን መካከለኛ የሚባል ነው"
ፋፎና ጨዋታው በተጀመረ በአራተኛው ደቂቃ ውስጥ ለኮትዲቮር የመሪነት ግብ ያስቆጠረ ሲሆን ክራስ ደግሞ በሁለተኛ አጋማሽ መጀመሪያ ላይ በአክሮባት ሁለተኛዋን ግብ ማስቆጠር ችሏል።
ጨዋታው የተካሄደው አመሻሽ ላይ ቢሆንም በነበረው ከባድ ወበቅ ምክንያት ተጨዋቾች ደክመው ታይተዋል።
ጋሴት "የሚቀር ስራ አለ። የውድድሩ መጀመሪያ ነው። ዛሬ ግን ተንፍሰናል...በጫና ውስጥ ስለነበርን ማሸነፋችን እንድነረጋጋ አድርጎናል" ብሏል።
ኮትዲቮር በቀጣይ ሀሙስ ከምዕራብ አፍሪካዋ የእግር ኳስ ኃያል ናይጀሪያ ጋር ትጋጠማለች።
ጋሴት አክለውም "የናይጀሪያን ጥንካሬ እናውቃለን። አርማዳ የተባለ ገራሚ አጥቂ አላቸው። በአፍሪካ ምርጥ ተጨዋች ነው" ብለዋል።
ጋሴት "ይህን ስለምናውቅ ጨዋታውን ከፍ አድርገን" እንጫወታለን ሲሉ ተናግረዋል።