በኮትዲቯር አስተናጋጅነት በሚካሄደው ውድድር ላይ 24 ሀገራት በ6 ምድብ ተደልድለዋል
34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከዛሬ ጥር 4 ጀምሮ እስከ የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።
ተወዳጁ የአፍሪካ ዋንጫ ከጥር 4 ጀምሮ ለአንድ ወር የሚካሄድ ሲሆን አዘጋጇ ኮቲዲቯር ስድስት ስታዲየሞችን አዘጋጅታለች፡፡
የውድድሩ መክፈቻ ጨዋታ 60 ሺህ ደጋፊዎችን በሚይዘው በአላሳን ኦታራ ስታዲያም በዛሬው ዕለት በኮቲዲቯር እና ጊኒ ቢሳው ጨዋታ ጅማሬውን ያደርጋል።
በኮትዲቯር አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ 24 ሀገራት በ6 ምድብ ተደልድለው ይፋለማሉ።