የልጃቸውን ደፋሪ በእሳት አቃጥለው የገደሉት እናት
ማሪያ ዴል ካርሜን ጋርሺያ የ13 ዓመት ሴት ልጃቸው አንቶኒዮ ኮስሞ በተባለ ሰው ተደፍራባቸው ነበር
የዘጠኝ ዓመት እስር የተላለፈበት ወንጀለኛው ከእስር ሲለቀቅ በልጃቸው ሊሳለቅ ሲሞክር በእሳት አቃጥለውት ህይወቱ አልፏል
የልጃቸውን ደፋሪ በእሳት አቃጥለው የገደሉት እናት
ማሪያ ዴል ካርሜን ጋርሺያ ስፔናዊት ስትሆን በቫሌንሲያ ከተማ ቬሮኒካ ከምትባል ሴት ልጇ ጋር ትኖራለች፡፡
አንቶኒዮ ኮስሞ የተሰኘው ሰው ደግሞ ጎረቤታቸው ሲሆን በሀይል በማስፈራራት ይህችን የ13 ዓመት ሴት ልጅ አሰገድዶ ይደፍራል፡፡
ይህ ሰውም ወዲያውኑ በፖሊስ ከተያዘ በኋላ ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን ተከትሎ በዘጠኝ ዓመት እስራት ይቀጣል፡፡
የተፈረደበትን የእስር ጊዜ ሳይጨርስ በጊዜ የተፈታው ኮስሞ ማሪያን በጎዳናዎች ለይ ካስቆማት በኋላ ስለ ልጇ ቬሮኒካ ያልተገቡ ቃላቶችን በማንሳት እንደሰደባት ተገልጿል፡፡
በልጇ መደፈር ብስጭት ላይ የነበረችው ማሪያም ከነዳጅ ማደያ ነዳጅ በማምጣት በሚዝናናበት ስፍራ በመግባት እላዩ ላይ ነዳጁን ከደፋች በኋላ በእሳት አቃጥላዋለች፡፡
ኮስሞም በደረሰበት የእሳት ቃጠሎ 90 በመቶ ሰውነቱ መጎዳቱን ተከትሎ ህክምና ላይ እያለ ህይወቱ አልፏል ሲል ሚረር ዘግቧል፡፡
ማሪያ በግለሰቡ ለይ በፈጸመችው ግድያ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን ጉዳዩ በመላው ስፔን ትኩረት መሳቡን ተከትሎ በርካቶች ከእስር እንድትለቀቅ በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል፡፡
አሜሪካ በአስገድዶ መድፈር ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በመርዝ ገደለች
እንዲሁም ማሪያ በልጇ ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት ለድባቴ እና ሌሎች የዐዕምሮ ህመሞች ተዳርጋለች፣ ለወንጀል ያነሳሳት ልጇን የደፈረው ሰው ነው፣ እድሜዋ ትልቅ መሆኑ እና ከዚህ በፊት ወንጀል ፈጽማ አለማወቋ ከግምት ውስጥ እንዲገባ እና ከእስር እንድትለቀቅ በሚጠይቁ የድጋፍ ሰልፎች ላይ የተነሱ ሀሳቦች ነበሩ፡፡
ማሪያ ወንጀል መፈጸሟ ከተረጋገጠ በኋላ የአምስት ዓመት እስር ከተላለፈባት በኋላ የእስር ጊዜዋን ቀለል ባለ መንገድ እንድታሳለፍ መወሰኑን ተከትሎ ቀን ቀን በነጻነት ወደ ፈለገችው ቦታ እንድትንቀሳቀስ ፈቃድ ተሰጥቷት ቅጣቷን ጨርሳለች፡፡