የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ስዊድን ኢስዋትኒ እና ፓናማ ቀዳሚዎቹ ሀገራት ተብለዋል
ሀገራት ለአስገድዶ መድፈር የሰጡት ትርጉም እና ወንጀሎችን የመመዝገብ ባህል በሀገራት መካከል የተለያየ መሆኑ ትክክለኛውን የወንጀል መጠን ለማወቅ አዳጋች እንዳደረገው ተገልጿል
የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ዓለም አቀፉ ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው ባወጣው መረጃ መሰረት ስዊድን፣ ኢስዋትኒ እና ፓናማ ከፍተኛ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከሚፈጸምባቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በዚህ ተቋም ጥናት መሰረት በዓለማችን 35 በመቶ ያህሉ ሴቶች ለጾታዊ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው የተባለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 10 በመቶዎቹ ብቻ ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስዱት ተገልጿል፡፡
ሀገራት ለጾታዊ ጥቃት የሰጡት ትርጉም እና ወንጀሉን የሚመዘግቡበት እንዲሁም የሚከላከሉበት መንገድ መለያየት በዓለማችን በትክክል ለጥቃት የሚጋለጡ ሴቶች ቁጥርን ለማወቅ አዳጋች አድርጎታል፡፡
በስዊድን ከ100 ሺህ ሴቶች ውስጥ 88ቱ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሲፈጸምባቸው በኢስዋትኒ 76 እንዲሁም በፓናማ ደግሞ 75 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሰለባ ይሆናሉ፡፡