አሜሪካ በአስገድዶ መድፈር ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በመርዝ ገደለች
ግለሰቡ የሞት ፍርድ ከተላለፈበት በኋላ በፍሎሪዳ ማረሚያ ቤት ተገድሏል
አሜሪካ በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ጥብቅ ቅጣት ከሚያስተላልፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት
አሜሪካ በአስገድዶ መድፈር ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በመርዝ ገደለች፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ከባድ ቅጣት ከሚያስተላልፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡
ሎራን ኮል የተባለው አሜሪካዊ የ57 ዓመት እድሜ ያለው ሲሆን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ይህ ወንጀለኛም የሞት ፍርድ የተላለፈበት ሲሆን በዛሬው ዕለት ታስሮ በነበረበት ፍሎሪዳ ማረሚያ ቤት ገዳይ መርዝ በመርፌ ከተወጋ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ግለሰቡ የገዛ እህቱን በመድፈር ወንጀል ከተመሰረተበት ክስ በተጨማሪም የፍሎሪዳ ዩንቨርሲቲ የሆነ የ18 ዓመት ወጣት ግድያም ተከሶ ጥፋተኛ ተብሏል፡፡
አሜሪካ የተያዘው 2024 ዓመት ከገባ ጊዜ ጀምሮ 13 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ የፈጸመች ሲሆን ይህም ሀገሪቱ የሞት ፍርድ በብዛት ከሚፈጸምባቸው የዓለማችን ሀገራት መካከል ከፍተኛዋ አድርጓታል፡፡
ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ቀጣች
አሜሪካ ካሏት 30 ግዛቶች ውስጥ 23ቱ የሞት ፍርድን የሚፈጽሙ ሲሆን ቀሪዎቹ ሰባት ግዛቶች ደግሞ የሞት ፍርዶችን ወደ እድሜ ልክ እስር ይቀይራሉ፡፡
እንደ ዓለም አቀፉ የስነ ህዝብ ፖፑሌሽን ሪቪው ጥናት ከሆነ በዓለም ላይ ካሉ ጠቅላላ ሴቶች መካከል 35 በመቶ ያህሉ ለጾታዊ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው፡፡
ይሁንና ጥቃቱን ከሚፈጽሙት ውስጥ 10 በመቶዎቹ ብቻ ህግ ፊት ቀርበው ውሳኔ ሲሰጣቸው ቀሪዎቹ በብዙ ምክንያቶች ተገቢውን ፍትህ አያገኙም፡፡
ከአሜሪካ በተጨማሪም ጥብቅ ህግ ያላቸው ሀገራት ሳውዲ አረቢያ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ቸክ ሪፐብሊክ፣ ሰሜን ኮሪያ እና ፓኪስታን ዋነኞቹ ናቸው።