"እዚህ የመጣነው ቁጥር ለማሟላት ሳይሆን ለመወዳደር ነው"- የሞሮኮ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን
በሴቶች የአለም ዋንጫ በመሳተፍ ከአረቡ አለም የመጀመሪያ የሆነው የሞሮኮ ቡድን የተጣለብኝን ኃላፊነት ለመሸከም ዝግጁ ነኝ አለ
ቡድኑ በዛሬው እለት የመጀመሪያ ጨዋታውን ከጀርመን ያደርጋል
የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጊዝላን ቸባክ ወደ ዓለም ዋንጫ ውድድር የመጣነው ቁጥር ለማሟላት አይደለም፤ በውድድሩ በመሳተፍ የመጀመሪያው የአረብ ሀገር በመሆናችን የሚጣልብንን ኃላፊነት እንወጣለን ብለዋል።
ቡድኑ በዛሬው እለት የመጀመሪያ ጨዋታውን ከጀርመን ጋር እንደሚያደርግ ሮይተርስ ዘግቧል።
ሞሮኮ የተሳተፊዎች ቁጥር ጨምሮ 32 በደረሰበት የሴት የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከጀርመን ጋር ታካሂዳለች። አሰልጣኝ ቸባክ ጉጉታቸው ከተሳትሮ በላይ መሆኑን ተናግረዋል።
ከአረቡ አለም ለመጀመሪያ ጊዜ በሴቶች የአለም ዋንጫ የተሳተፈው የሞሮኮ የሴቶች ቡድን አሰልጣኝ "እዚህ የመጣነው ቁጥር ለማሟላት ሳይሆን ለመወዳደር ነው" ነው በማለት ፍላጎታቸው ከተሳትፎ በላይ መሆኑን ገልጸዋል።
በቅጽል ስሙ የአትላንቲስ አንበሶች የሚባለው የሞሮኮ ሴት ብሔራዊ ቡድን በፈረንጆቹ 2022 ነበር ወደ አለም ዋንጫ ውድድር ማለፉን ያረጋገጠው።
"ጥሩ ምስል ለማሳየት ትልቅ ኃላፊነት መሸከም እንዳለብን እና የሞሮኮ እግር ኳስ ቡድን ያሳየውን የመሻሻል ውጤት ማሳየት እንዳለብን ይሰማናል። ይህ ለእኛ ትልቅ ውጤት ነው።" ሲሉ ተናግረዋል አሰልጣኝ ቸባክ።
ኳስ በሚወደድባት ነገርግን ሴቶች ብዙም በማይሳተፉበት ሀገር በአፍሪካ የሴቶች ዋንጫ ላይ ያሳዩት ብቃት ስማቸውን ከፍ አድርጎታል።
ኖሀይላ ቤንዚና በትልልቅ የሴቶች ውድድር ሂጃብ በመልበስ የመጀመሪያዋ ተጫዋች ትሆናለች። ፊፋ በሀይማኖት ምክንያት ሴቶች የእራስ መሸፈኛ እንዲያደርጉ የፈቀደው በፈረንጆቹ 2014 ነበር።
ሞሮኮ ዛሬ ከምትገጥማት ተቀናቃኞ ጀርመን በ70 ደረጃ አንሳ ትገኛለች። የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ለሞሮኮ ቀላል እንደማይሆን ተገምቷል።
የሞሮኮ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ኳታር በተካሄደው የአለም ዋንጫ ውድድር ሳይጠበቅ ትላልቅ ቡድኖችን በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜ በመድረሱ ከፍተኛ አድናቆት አትርፎ ነበር።