ኤአይ በፈጠራ ስራ ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተጽዕኖ
ኤአይ የሰው ልጅን የፈጠራ አቅምን ይቀንሳል
ኤአይ ለፈጠራ በብዙ መልኩ የሚያግዝ ቢሆንም በሰው ልጅን የፈጠራ ስራ ላይ የራሱ የሆኑ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል
ኤአይ በፈጠራ ስራ ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተጽዕኖ
አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ(ኤአይ) ለፈጠራ በብዙ መልኩ የሚያግዝ ቢሆንም በሰው ልጅን የፈጠራ ስራ ላይ የራሱ የሆኑ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል።
የሰው ልጅን የፈጠራ አቅምን ይቀንሳል፦
በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ(ኤአይ) ላይ የሚኖር ጥገኝነት የሰው ልጅን የፈጠራ ችሎታ እና ተፈጥሮአዊ እውቀትን ይገድባል። ኤአይ መፍትሄዎችን፣ ዲዛይኖችን ወይም ሀሳቦችን የሚያመነጭ ከሆነ ሰዎች ለፈጠራ የሚኖራቸው ዝንባሌ ይቀንሳል።
የውጤቶች አንድ አይነት መሆን፦
በተለይ አሁን ባሉ መረጃዎች ላይ ብቻ እንዲሰሩ የተደረጉት የኤአይ ሞዴሎች ወደአንድ አይነት ውጤት ይመራሉ። ይህ በኤአይ የመነጩ አዲስ ሀሳቦች ከባለፉት ፈጠራዎች ጋር ሊመሳሰሉ ይችላሉ፤ ይህ ደግሞ በፈጠራ ዘርፎች ያለውን ብዙኻነት ያቀጭጫል።
አድቫንስድ ኤአይን ከመጠቀም የሚያግዱ ፈተናዎች፦
ኤአይን የማበልጸግ እና የተሻሻለውን የኤአይ ሲስተም መጠቀም የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን እና የፋይናንስ ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በቂ የሆነ ፋይናንስ ይፈልጋል። ይህ ትንንሽ ኩባንያውች እና ግለሰቦች የፈጠራ ሰዎች ወደ ዘርፉ እንዳይገቡ ወይም እንዳይጠቀሙ እክል ይፈጥራል።
የፈጠራ መብቶች ጉዳይ ማወሳሰብ፦
በኤአይ የተገኙ የፈጠራ ስራዎች የእምሮአዊ ፈጠራ ባለቤትነት ጉዳይ ውስብስብ እንዲሆኑ ያደርጋሉ። በኤአይ የመነጩ የፈጠራ ሀሳቦች ወይም ስራዎችን በማን ባለቤትነት ይመዝገቡ የሚለው ግልጽ አይደለም። ይህ ግለሰቦች እና ኩባንያዎች የህግ ግጭት ያስነሳል በሚል ምክንያት ከኢንቨስትመንት እንዲርቁ ያደርጋቸዋል።
የስነምግባር እና የቁጥጥር መሰናክሎች፦
ቴክኒኖሎጂዎች እየዘመኑ ሲሄዱ፣ የስነምግባር ስጋቶች እና የቁጥጥር ስራዎች ፈጠራን ሊጎዱ ይችላሉ። የፈጠራ ባለሙያዎች ረጅም እና ውድ የሆኑ ውስብስብ ህግጋትን እና የሰነምግባር ደረጃዎችን ማሟላት ሊጠበቅባቸው ይችላል።
የስራ መፈናቀል እና የክሎት መሸርሸር፦
ቀደም ሲል በሰው ሲሰሩ የነበሩ ሰዎችን በኤአይ እንዲሰሩ ማድረግ ከስራ መፈናቀል እና የተወሰኑ ሙያዎችን እንዲሸረሸሩ ያደርጋል። ይህ የሰው ልጆች ባላቸው የተለያዩ ልምጆች እና ሙያዎች ላይ በተመሰረተው የፈጠራ ስራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።
ከፈጠራ ይልቅ ለአቅም መጨመር ትኩረት መስጠት፦
ኩባንያዎች ኤአይን ለፈጠራ ከማሳደግ ይልቅ የምርት አቅምን ለመጨመር ትኩረት አድርገው ሊጠቀሙበት ይችላል። ይህ አሁን ባለው አሰራር ላይ እንድናተኩር በማድረግ አዳዲስ ግኝቶች እንዳይኖሩ ያደርጋል።
አድሎአዊነት እና እኩል ያለመሆን፦
ኤአይ አሁን ባሉ አሰራሮች ላይ ያሉ አድሎዎችን ያስቀጥላል። ይህ ደግሞ አድሎአዊ የሆኑ ፈጠራዎች እንዲኖሩ ወይም በእኩልነት ላይ ያልተመሰረቱ ማህበራዊ መስታጋብሮች በፈጠራ ዘርፉ የተወሰኑ ቡድኖች እንዲገለሉ ማድረጉ የማይቀር ነው።