እስራኤል ኢላማዎችን ለመለየት ኤአይን ተጠቅማለች የሚለውን ሪፖርት አሜሪካ እየመረመረችው መሆኗን ገለጸች
መጽሄቱ እንደዘገበው ከሆነ የእስራኤል ጦር በአግባቡ በሰው ሳይታይ ኤአይን በመጠቀም በጋዛ ለግድያ የሚፈለጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለይቷል

የእስራኤል ጦር ግን የተጠረጠሩ አክራሪዎችን ለመለየት እና ኢላማ ለማድረግ ኤአይን መጠቀሙን አስተባብሏል
እስራኤል ኢላማዎችን ለመለየት ኤአይን ተጠቅማለች የሚለውን ሪፖርት አሜሪካ እየመረመረችው መሆኗን ገለጸች።
እስራኤል በጋዛ የቦምብ ጥቃት ለማድረስ ኢላማዎችን አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ(ኤአይ) የተጠቅማለች የሚለውን የሚዲያ ሪፖርት አሜሪካ እየመረመረችው መሆኗን የኃይትሀውስ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ክርቢይ ተናግረዋል።
ክርቢያ ከሲኤንኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት አሜሪካ በ+972 መጽሄት ላይ የታተመውን ይዘት ትክክለኛነት ገና አላረጋገጠችም። መጽሄቱ 'ላቨንድር' በተሰኘው አምዱ ላይ የእስራኤል የደህንነት ባለስልጣንን በምንጭነት ጠቅሷል።
መጽሄቱ እንደዘገበው ከሆነ የእስራኤል ጦር በአግባቡ በሰው ሳይታይ ኤአይን በመጠቀም በጋዛ ለግድያ የሚፈለጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለይቷል።
የእስራኤል ጦር ግን የተጠረጠሩ አክራሪዎችን ለመለየት እና ኢላማ ለማድረግ ኤአይን መጠቀሙን አስተባብሏል።
"የእስራኤል ጦር ሽብርተኞችን ለመለየት ወይም አንድን ግለሰብ ሽብርተኛ ነው ብሎ ለመተንበይ ኤአይን አልተጠቀመም። በኤአይ የሚሰበሰቡ መረጃዎች ኢላማ ለመለየት በሚደረግ ሂደት ለትንተና የሚረዱ ብቻ ናቸው" ብሏል ጦር ባወጣው መግለጫ።
ጦሩ ጨምሮ እንደገለጸው የጥቃት ኢላማ የሚለየው የሀገሪቱን እና አለምአቀፍ መመሪዎችን በመከተል ነው።
ክርቢይ በቃለ መጠይቃተቸው የእስራኤል የጸጥታ ካቢኔ ወደ ጋዛ የሚያስገባውን የእሬዝ ማቋረጫ ለመክፈት ወስኗል ስለሚለው ሪፖርትም ተጠይቀዋል።
ክርቤይ የሟቆረጫውን መከፈት "በበጎ የምንቀበለው" ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በትናንትናው እለት ከፕሬዝደንት ባይደን ጋር በጋዛ ጦርነት ጉዳይ መክረዋል ብለዋል ክርቢይ።
ኃይትሀወስ እንዳስታወቀው ባይደን እስራኤል በጋዛ በንጹሃን እና በእርዳታ ሰራተኞች ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ለማቆም ቁርጠኛ እርምጃ ካልወሰደች አሜሪካ ድጋፏን ታቆማለች ሲሉ ለኔታኔያሁ ነግረዋቸዋል።
ባለፈው ጥቅምት ወር ሀማስ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ 240 ሰዎችን ማገቱን እና 1200 ሰዎችን መግደሉን ተከትሎ እስራኤል እየወሰደች ባለው እርምጃ እስካሁን ከ32ሺ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸው የጋዛ የጤና ባለስልጣናት ገልጸዋል።