ማንቸስተር ዩናይትድን በ6 ቢሊዮን ዶላር ለመሸጥ ድርድር እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ
ማንቸስተር ዩናይትድ ከሼህ ጃሲም የጀመረው የብቻ የዋጋ ድርድር ሳይቋጭ፣ ከልላ ገዥ ጋር መደራደር አይፈቀድለትም
በክለቡ ትንሽ ድርሻ ያላቸው እና ክለቡን የሚቆጣጠሩት የግላዜር ቤተሰቦች ድርድሩን እያፈጠኑት እንደሆነም ተገልጿል
የእንግሊዙ እግርኳስ ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድ በኳታሩ ሼህ ጃሲም ቢን ሀማድ አል ታኒ ለሚመራው የባለሀብቶች ቡድን ራሱን በከ6 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ዋጋ ለመሸጥ እየተደራደረ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሮይተርስ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ድርድር እየተካሄደ መሆኑን እንዳረጋገጡለት ጠቅሷል።
በክለቡ ትንሽ ድርሻ ያላቸው እና ክለቡን የሚቆጣጠሩት የግላዜር ቤተሰቦች ድርድሩን እያፈጠኑት እንደሆነም ተገልጿል።
የኳታሩ ባለሀብት ያቀረቡት ዋጋ እንግሊዛዊ ቢሊየነር ጅም ራክሊፍ ካቀረቡት ዋጋ የተሻለ ነው ሲሉ የግሌዛር ቤተሰቦች ገልጸዋል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በርካታ ሸልማት ያሉት ክለብ ነው። ይህ ሽያጭ የሚከወን ከሆነ በስፖርት ዘርፍ ከተደረጉ ሽያጮች ትልቁ ይሆናል ተብሏል።
ማንቸስተር ዩናይትድ ከሼህ ጃሲም የጀመረው የብቻ የዋጋ ድርድር ሳይቋጭ፣ ከልላ ገዥ ጋር መደራደር አይፈቀድለትም። ነገርግን ይህ ጊዜ መቼ እንሚያበቃ አልተገለጸም።
እንደ ዲሎቲ ትንታኔጨከሆነ ክለቡ ባለው ሀብት ከእግርኳስ ክለቦች አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።