አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ በ50 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ትልቁ ተጠባቂ ጨዋታ በአርሰናል አሸናፊነት ተጠናቋል።
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በዛሬው ዕለት የተካሄደው የአርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታ በአርሰናል 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል።
አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ በ50 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።
የአርሰናልን የማሸነፊያ ጎሎቹን ኤዲ ኔኪታህ ሁለት ጎል እንዲሁም ቡካዮ ሳካ አንድ ጎል ለአርሰናል አስቆጥረዋል።
ማንችስተርን ከሽንፈት ያልታደጉ ሁለት ጎሎች ማርከስ ራሽፎርድ እና ተከላካዩ ማርቲኔዝ አስቆጥረዋል።