በዓለማችን የኑክሌር ጦር መሳሪያ የታጠቁ ሀገራት ብዛት ዘጠኝ ደርሷል
የዓለም የኑክሌር ወጪ በታሪክ ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደርሷል ተብሏል።
እንደ ስዊድኑ የሰላም ጥናት ኢንስቲትዩት ሪፖርት ከሆነ የዓለማችን ሀገራት ለኑክሌር ጦር መሳሪያ ያፈሰሱት ዓመታዊ ወጪ 83 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
አሜሪካ፣ ቻይና እና ሩሲያ ለኑክሌር ጦር መሳሪያ ፈሰስ የሚያደርጉት በጀት ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ተገልጿል። ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ እና ብሪታንያ በርካታ የኑክሌር ጦር መሳሪያ የታጠቁ ሀገራት ናቸው ተብሏል።
አሁን ላይ በዓለማችን 12 ሺህ 500 የኑክሌር ጦር መሳሪያ ያለ ሲሆን በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የዓለም ኑክሌር ጦር መሳሪያ ቁጥር እየቀነሰ እንደሆነ ተገልጿል።
በዓለማችን የኑክሌር ጦር መሳሪያ የታጠቁ ሀገራት ብዛት ዘጠኝ የደረሰ ሲሆን ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታንያ፣ ሕንድ፣ ፓኪስታን፣ እስራኤል እና ሰሜን ኮሪያ ደግሞ የታጠቁ ሀገራት ዝርዝር ነው።