ፖለቲካ
ሩሲያ፣ አሜሪካ በኑክሌር ልማት ጉዳይ ልታስተምረኝ አትችልም አለቸ
ሩሲያ ከ1991 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከግዛቷ ወጭ የኑክልር ጦር መሳሪያ የመላክ እቅዷን እንደምትገፋበት አስታውቃለች
የአሜሪካው ኘሬዝደንት ጆ ባይደን የሩሲያን ወደ ቤላሩስ የታክቲካል የኑክለር ጦር መሳሪያ የመላክ እቅድ ተችተዋል
ሩሲያ፣ አሜሪካ በኑክሌር ልማት ጉዳይ ልታስተምራት እንደማትችል ገለጸች።
የአሜሪካው ኘሬዝደንት ዶ ባይደን የሩሲያን ወደ ቤላሩስ የታክቲካል የኑክለር ጦር መሳሪያ የመላክ እቅድ ተችተዋል።
አሜሪካ ተመሳሳይ የኑክሌር መሳሪያዎች ወደ አውሮፖ ስትልክ ነበር ያለችው ሩሲያ፣ የአሜሪካን ትችት አትቀበለውም።
ሩሲያ ከ1991 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከግዛቷ ወጭ የኑክልር ጦር መሳሪያ የመላክ እቅዷን እንደምትገፋበት አስታውቃለች።
የቤላሩሱ ኘሬዝደንትም አሌክሳንደር ሉካሸንኮም መሳሪያዎቹ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዝደንት ባይደን ባለፈው አርብ እለት ሩሲያ የታክቲካል ኑክሌር ጦር መሳሪያ ወደ ቤላሩስ የመላክ እቅዷን እንደገፋችበት ሲረዱ በጽኑ ቁጣቸውን አሰምተዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ይህንን የሩሲያን እቅድ አውግዟል።
የሩሲያ ኢምባሲ በአሜሪካ፣ ሩሲያ እና ቤላሩስ ሉአላዊ ሀገራት ስለሆነ ደህንነታቸውን በማስጠበቅ ጉዳይ በጋራ የመስራት መብት እንዳላቸው ገልጿል።