ፕሬዝዳንት ፑቱን ሁለም ነገር በእቅዳቸው መሰረት እየሄደ መሆኑን ተናግረዋል
ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎችን ቤላሩስ ማስቀመጥ መጀመሯን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፑቲን አረጋገጡ።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታክቲካል የኑክሌር ጦር መሳሪያ ወደ ጎረቤቷ ቤላሩስ መጓጓዝ ላይ መሆኑን አስታውቃዋል።
የኑክሌር ጦር መሳሪያው በመጓጓዝ ላይ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ሁሉም ነገር በእቅዳቸው መሰረት እየሄደ መሆኑንኛ በወራ ውስጥ አሊያም እስከ ዓመቱ መጨረሻ ተጓጉዞ እንደሚያል አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ታክቲካል የኑክሌር የጦር መሳሪያ ወደ ቤላሩስ የመጓጓዝ ውሳኔያቸውን ያሳወቁት ከቤላሩስ አቻቸው አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ ነበር።
ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎችን ወደ ጎረቤት ሀገር የምታጓጉዘው በአሜሪካ የበላይነት የሚመራው ኔቶ ለዩክሬን በርካታ የጦር መሳሪያዎችን መስጠቱን በመቀጠሉ ነው።
ብሔራዊ ደህንነቴ አደጋ ውስጥ ከገባ የኑክሌር ጦር መሳሪያን እጠቀማለሁ የምትለው ሩሲያ ከአሜሪካ ጋር ከዚህ በፊት የነበራትን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ጥበቃ ስምምነት መውጣቷን አስታውቃለች።
የሩሲያ ውሳኔ እንዳሳሰባት የገለጸችው አሜሪካ አዲስ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ጥበቃ ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ከሰሞኑ አስታውቃለች።
ለአንድ ሳምንት ልዩ ዘመቻ በሚል የተጀመረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት አሁን ላይ 15ኛ ወሩ ላይ ይገኛል ።
በቅዝቃዜ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው ጦርነት አሁን ላይ ተፋፍሞ የቀጠለ ሲሆን ከሰሞኑ የኖቫ ካኮቭካ ግድብ ጥቃት ደርሶበት በርካታ የኬርሰን ግዛት ነዋሪዎች ቤታቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል።
በኖቫ ካኮቭካ ግድብ ላይ ለደረሰው ጥቃት ሁለቱም ሀገራት አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጣት እየተቀሳሰሩ ናቸው።