አዲሱ ፕሬዝዳንት ሂቺሊማ ለሀገሪቱ ቀጣይ እጣ ፈንታ ሁሉም እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል
በዛምቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ መሪው ሂቺሊማ አሸናፉ፡፡ ሂቺሊማ በስልጣን ላይ የቆይቱን ፕሬዝዳንት ኢድጋር ሉንጉን ጨምሮ ሌሎች 15 ተፎካካሪዎቻቸውን ማሸነፋቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡
በዛምቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በ156 የምርጫ ክልሎች ድምጽ የተሰጠ ሲሆን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በ155 የምርጫ ክልሎች የተገኙ ደምጾችን መሰረት በማድረግ ከሰአታት በፊት ውጤቱን ይፋ አድርገዋል፡፡
የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ኤሳው ቹሉ በተካሄድው ምረጫ ሂቺሊማ ከ50 በላይ ማለትም 2,810,757 ድመጽ እንዲሁም ሉንጉ 1,814,201 የሆነ ድምጽ ማግኘታቸው አስታውቋል፡፡
የናጠጡ ባለሀብት እንደሆኑ የሚነገርላቸው የ59 ዓመቱ ሂቺሊማ ባለፉት አምስት ምርጫዎች ተሳትፈው ሳይሳካላቸው ቢቀርም አሁን ላይ አዲስ ፕሬዝዳንት በመሆን የሀገሪቱ በትረ ስልጣን መጨበጥ ችሏል፡፡
ሂቺሊማ በምርጫ ዘመቻ ሲሉት እንደነበር ሁሉ የዛምባያን ኢኮኖሚ ሪፎርም የማድረግ ከፍተኛ የቤት ሰራ እንደሚጠበቅባቸውም ነው በመገለጽ ላይ ያለው፡፡
ምርጫው 16 የፕሬዝዳንት እጩዎች የተሳተፉበት ሲሆን ከተመዘገበው 7,023,499 የመራጮች ቁጥር 70 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች ድምጻቸው የሰጡበት ታሪካዊ ምርጫ ነውም ተብሎለታል፡፡
አዲሱ ፕሬዝዳንት ሂቺሊማ በትዊትር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት“ እኛ አንድ ሀገር፣ አንድ ህዝብ፣አንድ ዛምቢያ ነው፡፡ ለሀገራችን እና ለህዝባችን ስንል ለአንድ ዓላማ መተባበር አለብን፤ ከተባበርን ዛምቢያን ወደ ፊት ልንወስዳት እንችላለን”ብሏል፡፡
“ፈተናዎች የነበሩበት ቢሆንም ድሉ በሀገሪቱ የመንግስት ስርአት አዲስ ምእራፍ ነው” ያሉት ድግሞ የሂቺልማው ዩናይትድ ፓርቲ ፎር ዲቨለፕመንት የምርጫ ቅስቀሳ መሪ ጋሪ ንኮምቦ ናቸው፡፡
ንኮምቦ በምርጫው የተሳተፉትን ወጣቶች ያመሰገኑ ሲሆን: ውጤቱ ዜጎች በቀድሞ መንግስት የአስተዳደር ጊዜ እያሽቆለቆለ በነበረውን የሀገረቱ ኢኮኖሚ መማረራቸውን የሚያመላክት መሆኑን ለጋዜጠኞች ተናግሯል፡፡
ፓርቲው በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ቃል የገባውን ሁሉ ለመተግበር ዝግጁ ነውም ብሏል፡፡ውጤቱን ተከትሎ የሂቺሊማ ደጋፊዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡