የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ዙማ ጠበቃ ፕሬዘዳንቱ ችሎት የሚቀርቡበት ጊዜ እንዲዘገይ ጠየቀ
በእስር ላይ ያሉት የቀድሞው ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ሆስፒታል ገብተዋል
ጃኮብ ዙማ በያዝነው ሳምንት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል
የደቡብ አፍሪካ አቃቢ ህግ የቀድሞው ደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ችሎት እንዲዘገይ ጠየቁ።
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ በስልጣን ላይ እያሉ ፈጽመውታል በተባለ የጦር መሳሪያ ግዢ ተጠርጥረው በምርመራ ሂደት ላይ ነበሩ።
ጃኮብ ዙማ የተጠረጠሩበትን የሙስና ክስ አልፈጸምኩም በሚል ቢናገሩም ለምርመራው ቃላቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸዋል።
የእስር ጊዜያቸውን ከአንድ ወር በፊት የጀመሩት የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዙማ ባሳለፍነው አርብ ጀምሮ በህመም ምክንያት ወደ ሆስፒታል ተወስደው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡ይሁንና የቀድሞው ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ በዚህ ሳምንት በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ምርመራ በኩዋዙሉ ናታል ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን እንደሚሰጡ ይጠበቅ ነበር።
ዙማ መታመማቸውን ተከትሎም የሀገሪቱ አቃቢ ህግ እና የዙማ ጠበቃ የችሎት ጊዜው እንዲራዘም ወይም እንዲዘገይ ለፍርድ ቤት መጠየቃቸው ተገልጿል።የኩዋዙሉ ናታል ፍርድ ቤት ከአገሪቱ አቃቢ ህግ እና ከዙማ ጠበቃ የቀረበለትን የችሎት ይራዘም ጥያቄ እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም።
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ እስርን ተከትሎ በአገሪቱ በተከሰተ ሁከት የ354 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ በርካቶች ንብረታቸውን ተዘርፏል፤ የአገሪቱ መሰረተ ልማቶች መውደማቸው ይታወሳል።
የወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ በዚህ ሁከት ምክንያት የአገሪቱ የደህንነት ተቋማት ይሄ ሀኩት እና ዚረፋ እንደሚከሰት መረጃ እንዳልነበራቸው ገልጸው ተቋማቱ ዝግጁነት እንደሚጎላቸውም ተናግረው ነበር።
በዚህም ምክንያት ፕሬዚዳንቱ ባሳለፍነው ሳምንት የደህንነት ፤ኢኮኖሚ እና ጤና ሚኒስትሮች ላይ የካቢኔ ሹም ሽር አካሂደዋል።ፕሬዘዳንቱ ሹምሽር ካካሄዱባቸው የካቢኔ አባላት መካከል የመከላከያ፤ጤና እና የፋይናንስ ሚኒሰትሮቹን ከስልጣን በማንሳት አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመዋል።